የፍናፍንት ቀን ማስታወሻ፡ የተሳሳቱ ሀሳቦችን ስለማስተካከል

የፍናፍንት ማስታወሻ ወይም ከፍናፍንት ጎን የመቆም  (አብሮነት ማሳያ) ቀን በህዳር 29 ታስቦ ይውላል።

ይህም ቀን በፈረንሳዊ ፍናፍንት ሄርኩሊን አዴላዴን ባርቢን ልደት ቀን ታስቦ የሚውል ነው። ሄርኩሊን አዴላዴ ባርቢን በውልደት ላይ ሴት ተብላ ያደገች ፍናፍንት ስትሆን በቆይታ ግን በህጋዊ መንገድ ሙሉ የሰውነት ምርመራ በሁዋላ ወደወንድ የተቀየረ ግለሰብ ነው።

እንደ ኩዊር ማህበረሰብ ስለ ፍናፍንት ሊኖረን የሚገባንን ያህል በቂ እውቀት ሳይኖረን ስለቆየን  የነበረን ግንዛቤ ከአብዛኛው የሀገራችን ህዝብ የተለየ አልነበረም። 1.7% ያህል የአለም ህዝብ ፍናፍንት እንደሆነ ይታሰባል። በዚህም በሀገራችን ኢትዮጲያ ውስጥ ሊኖሩ እንደሚችሉም ምንም ጥርጥር የለውም።

እንደ ኮሚዩኒቲያችን የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ለፍናፍንት ሰዎች ቦታ መስጠት እና አረዳዳችንን ማስተካከል እንዲሁም እውቅና ላልሰጠነው ተፈጥሮ በቀናነት ራሳችንን ማዘጋጀት ነው።

እነዚህ ከታች ያሉት በተለምዶ ተሳስተው የሚነሱ ሀሳቦች ናቸው።

  1. ሁሉም ፍናፍንት ሰዎች በLGBTQIA አይገለፁም ወይም ኮሚኒቲው ውስጥ አይካተቱም። ቢሆንም እኛ LGBTQIAዎች ከሌላው ማህበረሰብ የተሻለ አረዳዳድ ሊኖረንና እና ፍላጎቶችን በሙሉ መቀበል አለብን። ይህ ቢሆንም ሁሉም ፍናፍንት ሰውን እንደ ኮሚኒቲያችን አባል መገመት የለብንም። 
  2. ፍናፍንት እና ትራንስጀንደሮች አንድ አይደሉም። አንዳንድ ፍናፍንት ሰዎች ትራንስ ሊሆኑ ይችላሉ ግን ሁሉም ናቸው ማለት አይደለም። ሁለቱም መገለጫዎች የሚያመሳስላቸው ልምዶች ቢኖሩም ችላ ሊባሉ የማይችሉ ዋና ዋና ልዩነቶች አሏቸው።
  3. ፍናፍንት መሆን ከፆታ መራቢያ በላይ ነው። እነሱም የፆታ መራቢያን አካትቶ፣ ክሮሞዞም፣ ሆርሞን እና ሁለትኛ ደረጃ የፆታዊ መገለጫዎች ያሉት ነው።
  4. ፍናፍንት ሰዎች በአለም ደረጃ ልክ በተፈጥሮ ቀይ ፀጉር ያላቸው ሰዎች ያሉትን ያህል ያሉ ናቸው። 
  5. አንድን ሰው አይታችሁ በትክክል ፍናፍንት ስለመሆናቸው የምታገኙት ማረጋገጫ ሊኖር አይችልም። በግምት ልታውቋቸው እንዳትሞክሩ።
  6. በፍናፍንት ግለሰቦች ዙሪያ የተቀመጠው ጥናት ሁሉም ፍናፍንት ሰዎች በዌስተርኑ አለም ላይ ብቻ እንደማይኖሩ ነው። እንደውም በመላው አለም የሚገኙና በተለያየ ዘር ውስጥ እንደሚኖሩ የታመነ ነው።
  7. ፍናፍንት አንድ መገለጫ እና ተለምዶ የለውም። ከ 35 በላይ የፍናፍንት መገለጫዎች እንዳሉ እና አብዛኛውን እንደኮመዩኒቲ በእኛም ዘንድ የምንጋራቸው መገለጫዎች ቢኖሩንም ሁሉም ፍናፍንት ግን አንድ አይነት መገለጫዎች እና ፈተናዎች ይኖሩታል ማለት አይደለም። 
  8. ሁሉም ፍናፍንት ሰዎች አንድ አይነት ሰውነት የላቸውም። በተደጋጋሚ ሰውነትን ስለ መቀበል ስናከብር በተፈጥሮ የተለያዩ የሆኑ አካሎች እንዳሉን ማስታወስ እንዘነጋለን። በተለይ ስለ ፍናፍንት ሰውነት ምንም አናወራም። ከዚህ በሁዋላ ግን የተሻለ እናድርግ።
  9. ፍናፍንት ሰዎችን ሁለት ብልት እንዳላቸው ሰዎች አትግለፅዋቸው። ይሄ መገለጫ ያለፈበትና ፍናፍንት ሰዎችን በትክክል እንዳንረዳ አወናብዶ የሚያስቀር መግለጫ ነው።
  10. የፍናፍንት ግርዛት (IGM) እንቅስቃሴን ለመደገፍ በእኛ ኮሚኒቲ ውስጥ ያለ ፍናፍንት ሰው የግድ ማወቅ አይጠቅባችሁም፤ ይሄንና መሰል ፅሁፎችን በማንበብ ግን በምትኖሩበት አካባቢ እና በማንኛውም ቦታ ሊኖሩ እንደሚችሉ በማሰብ አእምሯችሁን በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀት በቂ ነው።

Source: https://www.glaad.org/amp/debunking-10-intersex-myths

Leave a Reply