ኢትዮ ኩዊር ፓድካስት:“ቡችነት” ወይም “ወንዳወንድ” መሆን

“ቡችነት ወይም ወንዳወንድነት ከአለባበስ ወይም ከገፅታ ባለፈ ምንም ትርጉም የለውም…” ትላለች ማራኪ ስለወንዳወንድ ምንነት ስታብራራ

የዛሬው የፖድካስት ውይይታችን ኩዊር  “ወንዳወንድ” ሴቶች ላይ ያተኩራል። 

ማህበረሰባችን በተለምዶ “ወንዳወንድ” እያለ የሚጠራቸውን ሴቶች እንዴት ይረዳል? የእነሱስ ልምድ ምን ይመስላል?

ሁላችንም የአባታዊ ስርዓት የበላይነት ውጤት እንደመሆናችን ኩዊር ሰዎችም ከዚሁ ስርዓት ያመለጡ አይድሉም:: የምንኖረው ወንድነትን ከጀግንነት፣ ከመሪነት እና ከሰጪነት ጋር በተቃራኒው ደግሞ ሴትነትን ከተቀባይነት እና ከተመሪነት ጋር የሚያያይዝ ማህበረሱብ ውስጥ ነው:: ይህ ስርዓት በሁሉም የእለት ተእለት ኑሯችን ላይ ጣልቃ ሲገባ ይታያል፤ በፍቅር ግንኙነቶችም ላይ እንዲሁ::

“ወንዳወንድ ስለሆንሽ ሂሳብ መክፈል ይጠበቅብሻል” ትላለች ፍጹም ስላለው ባህላዊ የስርዓተ ፃታ ክፍፍል ስታወራ…

ከአራት የኩዊር ሴቶች ጋር ባደረግነው ቆይታ እነዚህን እና የመሳሰሉትን የስርዓተ ፃታ ክፍፍሎች፣ በእየለት ስለሚመጡባቸው ገጠመኞች እና በምን መልኩ እነዚህን ያልተፈለጉ አረዳዶች መቅረፍ እንደምንችል አጫውተውናል:: 

ይህ ውይይት ስለስርዓተ ፆታ የተሻለ መረዳት እንዲኖረን፣ እንዲሁም ከዚህ ማህበረሰብ እንደመውጣታችን በዚሁ ዙሪያ ያሉብንን የተሳሳቱ መረዳቶች መለስ ብለን እንድንመከት እና ራሳችንን እንድንፈትሽ ያደርገናል:: 

ተጋበዙልን!

Leave a Reply