ኢትዮ ኩዊር ፓድካስት: ቀና የወሲብ አስተሳሰብ

“ሃገራችን ላይ የተለያዩ የውይይት መድሩኮች ቢኖሪም ስለወሲብ የሚያወያይ ወይም በጥናት የታገዘ ግንዛቤን የማስጨበጫ ውይይቶች የሉም:: “በብዙ መንገድ uncomfortable የሚያደርጉንን [ምቾት የማይሰጡንን] ነገሮች መንካት አንፈልግም::”  ይላሉ ከእንግዶቻችን አንዳቸው  

“… ማህበረሰባችን ያለውን አረዳድ ስትግልፅ “[Sex education] ህፃናትን ት/ቤት ውስጥ እናስተምራቸው የሚባለው idea ራሱ ቢመጣ አብዛኛውን ወላጅ ሊሆን ይችላል፣ አስተማሪ፣ ማህበረሰብ የሚቃረነው ነገር ነው ምክንያቱም ይሄንን ትምህርት የሚያዩት ራስን እንድማወቂያ… ሳይሆን እንደሚያበላሽ ነገር ነው::” ይላሉ ሌላኛዋ እንግዳችን:: 

ወሲብን እንደነውር እና የተደበቀ ነገር እና ፍረጃ የተሞላበት እድርጎ ከሚያይ ማህበረሰብ መምጣታችንን እነዚህ ከፖድካስት ውይይታችን የተወሰዱት ቅንጭብጫቢ ሃሳቦች ያስታውሱናል:: ታዲያ እንደኩዊር ማህበረሰብ ከዚህ የተሻለ አረዳድ እንዴት ማምጣት እንችላለን? 

“እንዴት ነው እዚህ community [ማህበረሰብ] ውስጥ መደማመጥ የምንችለው… protect ልንደራረግ የምንችለው.. እንጂ እርስ በራሳችን [የምንፈራረድ] ከሆነማ እንዴት አድርገንስ ነው protection ሌላ ቦታ የምንፈልገው?” ይላሉ ሌላኛዋ እንግዳችን:: 

በዛሬው ፖድካስታችን ላይ እንግዶችቻን በወሲብ ዙሪያ በኩዊር ማህበረሰብ ላይ ያሉትን ችግሮች፣ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ያለፉቃድ ምስሎችን ስለመላላክ እንዲሁም በግንኙነት ላይ ስለሚገቡ ግልፅ ውይይቶችን በመዳሰስ ቀና የወሲብ አስተሳሰብን እንድንለማመድ ያበረታቱናል:: 

ተጋበዙልን!

1 thought on “ኢትዮ ኩዊር ፓድካስት: ቀና የወሲብ አስተሳሰብ”

  1. እኔ ተፈጥሮን የማከብር እና የምቀበል ሰው ነኝ ሰው ባለው ተፈጥሮ መደሰት መቻል አለበት እንጂ አንገት መድፉት የለበትም ብዬ አምናለሁ ለምሳሌ እኔ ትራንስ የሆነችን ሴት ባገባ ደስ ይለኛል እየፈለኩም ነው

Leave a Reply