የኢትዮኩዊር ፖድካስት: የስርዓተ ፆታ ማንነት እና አቀራረብ

በቅርብ በነበረን የLBQ ስብስብ ላይ ስለማንነታችን በነበረ ውይይት መሃል አንድ ሰው “እኔ ነን ባይነሪ ነኝ” አሉ:: በክፍሉ ዝምታ ሰፈነ፤ አብዛኞቹም የግርታ ፊት ነበራቸው:: በመጨረሻ አንድ “ወንዳወንድ” ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ሴት ደፈር ብላ “ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?” ብላ ጠየቀች::

በLBQ ማህበረሰብ ውስጥ የስርዓተ ፃታ ማንነት እና አቀራረብ ብዙም ውይይቶች አይታዩም:: አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል በጣም ሁለትዮሽ የሆነ የስርዓተ ፃታ አመለካከት ነው ያለው እናም ግልፅ የሆነና ከፍረጃ የፀዳ ውይይት የማግኘት እድሉ የለውም::

ይህ አዲሱ የኢትዮኩዊር ፖድካስት ለውይይት እንደሚጋብዛችሁ ተስፋ እናደርጋለን:: ሁለት ነንባይነሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ስለስርዓተ ፃታ ጉዞዋቸው እና የስርዓተ ፃታ ማንነትን አጫውተናል::

ስለነንባይነሪ ሰዎች ስናወራ ተውላጠ ስም  ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን እና የአማርኛው ቋንቋ ከሚገድበን ይልቅ በእውነታዎቻችን ላይ ተመስርተን ማመቻቸት እንደምንችል ጨምረን ተወያይተናል::

ለበለጠ ውይይት እንደሚጋብዛችሁ ተስፋ እናደርጋለን::

Leave a Reply