ኢትዮ ኩዊር ፖድካስት : ባይሴክሽዋል ጠልነት በLGBTQ+ ማህበረሰብ

በሚያሳዝን ሁኔታ በኢትዮጵያ LGBTQ+ ማህበረሰብ ውስጥ ባይሴክሽዋል ጠልነት በጣም የሰፋ ነው፤ ምን ያህል ባይሴክሽዋል ማህበረሰብ ላይ ተፅዕኖ እንዳለው ለመረዳት ሩቅ መሄድ አይጠበቅብንም:: የዚህ ሳምንት የኢትዮ ኩዊር ፖድካስት በዚህ ዙሪያ ወደጠለቀ ውይይት እንድንገባ መንደርደሪያ መሆን ይችላል::

እንግዶቻችን በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ የተሳሳቱ አረዳዶች ማለትም “ባይሴክሽዋሎች ወንድ መምረጥ ስለሚችሉ ለነሱ ቀላል ነው” ከሚል እስከ “ወንድ እስኪያገኙ ነው ከሴት ጋር ዝም ብለው ጊዜ የሚያሳልፉት” እና እንደተቃራኒ ፃታ አፍቃሪያን ተመሳሳይ ገድ አላችው ድረስ ይሄዳል:: ባይሴክሽዋል ሰዎች በተከታታይ መገለል ይደርስባቸዋል በመሆኑም ብዙ ጊዜ ኩዊር ቦታዎች ላይ ብዙ አቀባበል አይደረግላቸውም ወይም አቀባበል ቢደረግላቸውም በሚጎዱ ባይሴክሽዋል ጠል አስተያየቶች ይዥጎደጎዳሉ፤ እነዚህ አስተያየቶች አብዛኛውን ጊዜ በኩዊር ሰዎች አይጠየቁም ወይም አይፈተሹም::

ባይሴክሽዋል ጠልነት ምን ማለት ነው? ባይሴክሽዋል ጠልነት ባይሴክሽዋል ሰዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? በLGBTQ+ ማህበረሰብ ውስጥ ሁሉን አካታች የሆነ ቦታን ለመፍጠር ተግዳሮቶቹ ምንድን ናቸው?

መልስ ላይኖረን ይችላል ነገር ግን ይህ ውይይት ለዚህ ጥያቄ ጥሩ እና ወሳኝ መስመር መጀመሪያ ይሆናል::

Leave a Reply