አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: ደፋር ነፍሳት

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

ከታች የተቀመጠው ከረዥም የኢሜል መልዕክት የተቀነጨበ ነው፤ በኢትዮጵያ የLGBTQ+ ማህበረሰብን እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ያስሳል

“ለኩዊር አፍሪካውያን ማህበራዊ አንቂዎች እና መብት ደጋፊዎች ትልቅ ክብር አለኝ:: ጠመንጃ ተደኖብሽ አለመፍራትን አስበሽዋል? “ተኩሱ! ከማምንበት እና ከማንነቴ ንቅንቅ አልልም::” ማለት መቻል? ምንም እንኳን በህይወት ላይ አደጋ ቢኖረውም ለምታምኝው ነገር ፀንተሽ መቆም? አንድ ጓደኛ አለኝ ይሄንን አደጋ ከመውሰድ በፊት ማህበረሰብን የመፍጠር አስፈላጊነትን የምታስታውሰኝ:: እንዴት ነው አንድ ሰው ማህበረሰብ መገንባት የሚችለው?

Leave a Reply