በአውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር መሰረት አዲሱን አመት ለምታከብሩ …

ከኡጋንዳ መሪዎች “LGBTQ ሰዎች ተቃራኒ ፃታ አፍቃሪያንን ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪያን ማድረግ ይፈልጋሉ በሚለው የቆየ የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪያን ቅዥት ላይ በመመስረት ማንቂያዎችን ማንሳት” በጋና የቀረበው “እስከ ዛሬ እጅግ የከፋ የፀረ LGBTQ ህግ” ጨምሮ ላለፉት አመታት በአፍሪካ LGBTQ+ ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ቀጥሏል።

ማህበራዊ አንቂዎች እና የተለያዩ LGBTQ+ ሰዎች በማንነታቸው እና በሚወዱት ምክንያት በመወንጀል ህይወታቸውን አጥተዋል::  ብዙዎች በወሲባዊ እና ስርዓተ ጾታ ማንነታቸው የተነሳ ነፃነታቸው ሲታፈን አይተዋል። በተለያዩ ተቋማት የሚደገፈው ጥላቻ በህይወታችን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን ይቀጥላል ፣ እና እኛ ያለማቋረጥ በአፍሪካ ህዝባችን ላይ ለሚደርሱት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንደ ዋነኛ ምክንያት ተደርገን እንዘለፋለን:: 

ይህ በአፍሪካ ውስጥ  ያለነውን LGBTQ+ ማህበረሰብ  አባላት ሊያስደነግጠን  ይችላል ነገር ግን  በፅናት እና ማንነታችንን በሚያስከብር መልኩ ህይወታችንን መምራት መቀጠል ይኖርብናል:: 

በአውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር መሰረት አዲሱን አመት ለምታከብሩ፣ ወደ አዲሱ አመት ስትገቡ ይህ የተስፋ መልእክታችን ነው። መገዛትን መቃወማችንን የምንቀጥል ጠንካራ ሰዎች መሆናችንን እናስታውስ።  ህይወታችንን በእውነት እና በታላቅ ክብር መኖራችንን እንቀጥላለን።

መልካም በዓል

Leave a Reply