አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: ከኢትዮጵያ መትረፍ

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

ከታች የተቀመጠው ከረዥም የኢሜል መልዕክት የተቀነጨበ ነው፤ በኢትዮጵያ ኩዊር ሰው ሆኖ ለመኖር ያለውን ትግል ይዳስሳል

እዚህ ሃገር ያለው ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ እና ትራንስ ጠልነት አይታመንም:: በሴቶች የመናገር ድፍረት ላይ ያለው ንዴት መቋቋም የሚቻል አይደለም። ምንም አላሰማምረውም፥ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ጦርነት ነው:: መናገር ደግሞ ከትልቅ ችግር ጋር ነው የሚመጣው እና ለዚህም በጭቆና የሚመጣ የስሜት ቀውስ ውይይት በደንብ ይገባኛል።

በተቃራኒ ፃታ አፍቃሪ ልከኝነት ብቻ በሚታይበት አለም ሌይ ስርዓተ ፃታን መፈተሽ፣ መመርመር እና የተሰመረውን መስመር መሞገት ለትልቅ ጥቃት ያጋልጣል፤ እንደጭኔም ይወሰዳል።  ይሄንን አደጋ ለመቀነስ ወይም ለመቻል መንገዶች ያገኘው መስሎኛል:: እርግጥ ተፅዕኖ አለው.. ህመሙን ለመቀነስ መንገዶችን ተምሬያለሁ:: ዮጋ እና የጥሞና ጊዜን በማዘውተር እንደገና ወደቦታዬ መመለስ እና የትኛውንም ጥላቻ በግል ባለመውሰድ  ራሴን እጠብቃለሁ። ምት ያላቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ብስጭትን ለመወጣት ምርጥ ናቸው:: መልካም ሰዎች በዙሪያዬ አሉ… ነገር ግን በሃለኛው ጮኼ ከዚህ አገር ውልቅ ማለት የሚያምረኝ ቀናት አሉ።”

Leave a Reply