ከደጋፊዎቻችን ጋር በተደረገ ውይይት ዙሪያ አስተያየት

እንደ አንድ ኩዊር ሰው ከደጋፊዎቻችን ጋር የነበረንን ውይይት እንዴት ያዩታል ለሚለው ጥያቄ ምን መልስ አሎት? እስኪ በetqueerfamily@gmail.com ያጋሩን። ለመነሻ ያህል የአንድ ሌዝብያንን አስተያየት ከስር ያንብቡ:-

“የተነሱት ሃሳቦች፣ ግንዛቤያቸው እና እውቀታቸው በጣም ደስ የሚል ነው። ማህበረሳባችን ውስጥ ነን ከሚሉት ጋር በጣም እኩል ወይንም በበለጠ እውቀት ነው ያላቸው እና በጣም ደስ ብሎኝ ነው ያዳመጥኩት። ተመስጬ ነው ያዳመጥኩት።”

“[አንዷ ተሳታፊ እንዳለችው] እነሱ እና እኛ መባል የለበትም የሚለውን ሃሳብ እኔም የምጋራው ነው። እነሱ እና እኛ ሲባል በተለያየ አለም ያለን ሰዎች መሆናችንን ይገልፃል፤ ማለትም እኛ LGBTQ ማህበረስብ ውስጥ ያለን ሰዎች የተለየን ወይንም የተለየ ማህብረሰብ ውስጥ ያለን ያስመስለዋል።”

Leave a Reply