ዝምታን መስበር: አለም አቀፍ የሆሎኮስት መታሰቢያ  ቀን

ለመጀመሪያ ጊዜ የLGBTQ ተጠቂዎች በናዚዎች የተገደሉትን በማስታወስ በቡንዴስታግ፣ የጀርመን የታችኛው የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ልዩ ትኩረት ነበሩ። የናዚ አገዛዝ ሰለባዎች ዓመታዊ መታሰቢያ የሚካሄድበት ቀን ዓለም አቀፍ የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን በሚከበርበት እለት ነው።

“በሆሎኮስት 6 ሚሊዮን የሚጠጉ አይሁዶች በናዚዎችና በተባባሪዎቻቸው ተደምስሰዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ጌ፣ ሌዝቢያን፣ ባይሴክሽዋል እና ትራንስጀንደር ሰዎች በናዚዎች ታስረው ተገድለዋል፣ሌሎች ፣እንደ ሮማ እና የሲንቲ ብሄረሰቦች እና የአእምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች በናዚ አገዛዝ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተገድለዋል።”

LGBTQA ሰዎች በሆሎኮስት ታሪክ ውስጥ እንዳልተካተቱ ብዙዎች ተከራክረዋል። በTIME መጣጥፍ ላይ እንደተገለጸው፣ መገፋቱ እና እንግልቱ ከነጻነት በኋላ ብዙ ዘልቋል። “እውነታው ግን ከናዚ ጭቆና ለተረፉት ኩዊር ሰዎች 1945 ምንም ዓይነት ነፃነት አላመጣም። ይልቁንም ስልታዊ የሆነ መገፋት ሆን ተብሎ የመታፈን ሂደት መጀመሩን ያመለክታል፤ ከታሪክ ሆን ተብሎ የመስረዝን ወይም የመቀነስን ውጤት ያመጣ መገፋት።

በዚህ አመት መታሰቢያ ላይ በLGBTQ ተጠቂዎች ላይ ያለው ትኩረት ፣ የስርዓተ-ፆታ እና ወሲባዊ ማንነትን መገፋት በማጉላት በማህበረሰቡ ውስጥ የብዙዎችን ስቃይ ዝምታን መስበሩ ትልቅ ነገር ነው ምክንያቱም ተስፋን ይሰጠናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ተገፍተን እንደምንኖር ስርዓተ ፃታ እና የተለያየ ወሲባዊ ማንነት እንዳለን ማህበረሰብ፣ ይሄ ነገር በፍፁም የማይቀየር እና ሁሌም ተገፍተን እንደምንኖር ማሰብ ቀላል ነው። ታሪክ ግን ተስፋ እስካልቆረጥን ድረስ ነፃነት የሚቻል ነገር መሆኑን ያስተምረናል።

Leave a Reply