የፍቅር ግንኙነት: እንደኩዊር ሴት የፍቅር ግንኙነት ምን ይመስላል?

ብቻዬን ስሆን ያለምንም ጥርጣሬ ሙሉ ለሙሉ ራሴን የሆንኩ ሰው ነኝ፤ ነገር ግን ከፍቅር አጋር ጋር ስሆን እደነግጣለሁ ምክንያቱም ለእነሱ እፈራላቸዋለሁ ከኔ ጋር ስለሆኑ ሰዎች እንዲተናኮሏቸው ወይም እንዲሰድቧቸው አልፈልግም። የሚረብሽ እና ግር የሚል ስሜት ነው።

አሁን ላይ የምከተላቸው ሶስት ህጎችን አውጥቻለሁ (በፍቅር ግንኙነት ዙሪያ)፥ የመጀመሪያው ራሳቸውን ካልቻሉ ሴቶች ጋር የፍቅር ግንኙነት አይኖረኝም፣ ሁለተኛው ከማንነታቸው ጋር ሙሉ ለሙሉ ካልታረቁ ሴቶች ጋር የፍቅር ግንኙነት አይኖረኝም ሶስተኛው ደግሞ መንፈሳዊ ሰላም የሌላቸው ሴቶች ጋር የፍቅር ግንኙነት አልጀምርም። ይሄንን ህግ ያወጣሁት ከበፊት ገጠመኖች በመነሳት ነው፤ ገሃነምን አይቼ የተመለስኩባቸው ገጠመኞች ናቸው። ስለዚህ አሁን ላይ እነዚህ ሶስት ነገሮችን ካላሟላች ሴት ጋር የፍቅር ግንኙነት አልመሰርትም:: ይገባኛል ከምንኖርበት ሃገር አንፃር እነዚህን መጠየቅ ብዙ ነው፥ የምናምነው፣ ባህሉ እና ያደግንበት ሁኔታ እንዲሁም የሃይማኖቱ ሆሆይታ ራሳችንን የምናይበት መንገድ ምናምን ነገር ግን እንደበፊቱ ሰላሜን መስዋዕት ላደርግ አልችልም፤ ከሁሉም በላይ ትልቅ ዋጋ የምሰጠው ነገር ነው።

Leave a Reply