አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: ግንዛቤዎችን ማሰስ

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

ከታች የተቀመጠው ከረዥም ውይይት የተቀነጨበ ነው፤ በአዲስ አበባ ኩዊር ሰው ሆኖ ለመኖር ያለውን ትግል ይዳስሳል።

“እና እውነት ለመናገር ፣ የአንቺ እናት በጣም ትክክለኛ ነጥብ ያላት ይመስለኛል። እኔ በተለምዶ ወንዳወንድ የሚባለው የስርዐተ ጾታ ነው ያለኝ። እኔ ኩዊር ነኝ እናም አዲስ ጎዳና ላይ ስርዐተ ጾታዬን እንደፈለኩት ለመሆን ሙሉ በሙሉ ቀላል ነው ማለት አልችልም። ነገር ግን ከስርዐተ ጾታ ባለፈ ማየት ስለሚችሉ ሰዎችም የሆነ ነገር ማለት አንበል። ስለዚህ በአንድ በኩል፣ ምናልባት ከአምስት፣ ከስድስት፣ ከሰባት ዓመታት በፊት ሰዎች እንደ “ወንዳወንድ” ወይም እንደዛ ነገር ብለው ነበር የሚረዱኝ። አሁን፣ የተረዳሁት ግን ሰዎች እኔን የሚያዩኝ እና እንደ ኩዊር፣ እንደ ሌዝቢያን ወይም እንደ ዳይክ ወይም ሌላ ነገር ነው።

ምክንያቱም ከ10 አመት በፊት ሰዎች ስለተለመደ የሌዝቢያን ወይም ዳይክ ወይም ኩዊር የመሆን አመለካከት ያወሩ ነበር። አሁን ግን በመገናኛ ብዙኃን እና በሰዎች ዘንድ እየታየን ነው፤ ሰዎች ደግሞ ፌስቡክ ቲክቶክ እና የመሳሰሉት ላይ አሉ። ስለዚህ ስለኩዊርነት የሚደረገው ውይይት፣ ምንም እንኳን በጣም ውስን በሆነ መልኩ፣ በተለምዶ “የሴትነት ባህሪ” ያላቸው ወንዶች እና የተለመደ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሴት ዙሪያ ነው። መሃል ላይ ያለ ውይይት የለም። እና ሁለትዮሽ ውጪ ያለ ስርዐተ ጾታ፣  ትራንስ ወይም ሌላ ነገር እንደውይይት ሲመጣ ሰዎች ግር ይላቸዋል። ነገር ግን ሌዝቢያን ላይ እንኳን ስናነሳ: በኢትዮጵያ ያለው የስርዐተ ጾታ እና ወሲባዊ ማንነት አረዳድ በምዕራቡ ዓለም ምናልባትም ከ30 ዓመታት በፊት የነበረ አረዳድ ነው።

እና እናትሽ እያለች ያለችው ስጋት እና ደህንነት አለመሰማት፣ አምስት ዓመት በፊት ከነበረኝ የበለጠ አሁን ይሰማኛል።”

Leave a Reply