አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: ሃይማኖት፣ ንዴት እና እኔ

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

ከታች ያለው ሃሳብ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ኩዊር ሰው ጋር በኩዊርነት እና ሃይማኖት ዙሪያ ከነበረ ረዥም ውይይት የተቀነጨበ ነው።

“ስለሃይማኖት ባሰብኩ ቁጥር ዞሮ ዞሮ ወደ ንዴት ነው የሚወስደኝ። ስሜቴን በጥልቅ ምን እንደሆነ ጊዜ ወስጄ አላሰብኩበትም ግን በጣም የንዴት ስሜት ይሰማኛል። አንዳንዴ ጭራሽ ድባቴን ይፈጥራል:: እንቅልፍ ያሳጣኛል:: በጣም ግራ የመጋባት ስሜት ይሰማኛል። ትክክለኛ ውሳኔ እንደወሰንኩ እርግጠኛ አይደለሁም:: እና በቃ ምላሼ መናደድ ነው:: ሃይማኖት ላይ ትልቅ ንዴት አለብኝ፣ ቤተ እምነቱ እና ሰው ሰራሽ ነገሩ ሁሉ።

ከምንም በላይ በጣም የሚወተውተኝ ቤተሰብ አይቀበለኝም የሚለው ፍራቻ ነው።”

Leave a Reply