ማህበረሰብ በመፍጠር ላይ ሀሳቦች

“ይሄንን ማህብረሰብ ሰፋ ለማድረግ ብንሰራ ጥሩ ነው ።ምክንያቱም እኔ ራሴ  አዲስ አበባ ተወልጄ ያድኩት ግን ክፍለ ሃገር ነው ። እና ክፍለ ሃገር በነበርኩበት ሰዓት በጣም ብዙ የእኛ ማህበረሰብ አሉ፣ በጣም ሌዝቢያኖች አሉ ግን ጓደኛ ፈልገው  ወይ ሰው ፈልገው እንኳን አያገኙም። ይሄንን ነገር ከእርግማን ጋር አያይዘውት እየሄዱ ነው። አዲስ አበባ ስትመጪና እና ሌላ ሴቶች ስታገኚ ግን ለካ ይሄ ነገር የእውነት ነው  ነው የምትይው። ወንዶች ጥሩ እየሄደላቸው ነው ሴቶች ግን ወደኋላ እየቀረን ስለሆነ በየሙያችን ብንተባበበር የሆነ ነገር ማድረግ ይቻላል። በእርግጥ ስድብ ይመጣል ግን አሁንም እየተሰደብን ነው መሰደባችን ላይቀር ይስደቡን እኛ ደግሞ ስራውን በደንብ እንስራ።

ጌ ጓደኞች አሉኝ። የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው እና እነሱ ቦታ ጋር እየሄድኩኝ ስዕሎቼን እሰራለሁ ማንም  አይናገረኝም ፤ እንደውም ያደንቁኛል፤ አንቺ ልጅ እየጎበዝሽ ነው አይነት ነገር። ሴቶችም ይኖራሉ ብዬ አስባለሁ የተለያየ ታለንት ያላቸው  እና ህብረት ኖሮን አብረን ብንሰራ በጣም ደስ ይለኛል። ምክንያቱም ፈቃደኛ ነኝ!”

Leave a Reply