ንስንስ፥ አባት ለኩዊር ልጁ ያለው ፍቅር

በቅርብ የወጣው የንስንስ እትማች አጋሮች ላይ ያተኮረ ነበር። ቃለ መጠይቅ ካደረግንላቸው ሰዎች መካከል አንዱ የኩዊር ልጅ አባት የሆኑትን አቶ አለማየሁን ነው። ስለ እሳቸውም ሆነ ስለ ሌሎች ሰዎች ተጨማሪ  ለማንበብ የንስንስ ሰባተኛ እትም አንብቡ።

ጥያቄ ከኩዊር ኢትዮጵያ፥ የእርስዎ አመለካከት ከብዙ ኢትዮጵያዊ  ለየት ያለው ለምን ይመስሎታል? ልጅዎትን በአንዴ መቀበል የቻሉት ለምን ይመስሎታል?

አለማየሁ፡ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው፤ መቼስ የእኛ ሀገር ባህል በጣም በጣም በጣም እንግዳ (ስትሬንጅ) የሆነ ባህል ነው፡፡ ከባድ የሆነ ነገር ነው እና በጣም ይገርመኛል፣ የኔን ትንሽ ለየት የሚያደርገው ብዙ ግዜ በልቤ ነው ሃይማኖቴ ያለው፣ በእየሁዱ እየሄድኩ አንደዚህ ነው ጌታዬ አንደዚህ አድርግ የሚባል ነገር አላውቅም፣ የማውቀው ጥሩ ነገር በመስራት፣ እውነተኛ በመሆን ነው እምነቴ ለእኔ፡፡ የቸርች ሰው አይደለሁም፣ ኮንሰርቫቲቭ አይደለሁም፣ አውቃለሁ አባትና እናቴ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ናቸው፡፡ የስላሴን ፀዲቅ በየአመቱ አንድ ግዜ ይዘክራሉ፡፡ እና ያደግኩት አንደዛ ነው እና ግን ብዙውን ግዜ ያሳለፍኩት አሜሪካ ውስጥ ስለሆነ የአሜሪካንን ሶሳይቲ የአሜሪካንን ካልቸር ሞር እያወቅኩት መጥቼ በጣም ብዙዎቹ ሆሞሴክሹዋል ሰዎች ጋ አብሬ ሰርቼ ከዛ የተለየ ማሰብ አልቻልኩም፡፡ እና ይሄንን ብዙ ስላወቅኩ አሜሪካ ውስጥ የሚደረገውን የሶሻል አኗኗር የሰውን አኗኗር፣ የጥቁር፣ የነጩን፣ የጌዩን፣ የሌዝቢያኑን የሁሉም አይነት አኗኗር በአሜሪካ ውስጥ አለ፡፡ እና እንዳጋጣሚ እኔ ላይ ቢሆን ምን አደርጋለሁ? እና ምንም የተለየ የማደርገው ነገር የለኝም ምክንያቱም በየቀኑ የምሰራበት ቦታ አገኛቸዋለሁ፣ጓደኞቼ ናቸው እና የኔም ልጅ ከእነሱ የተለየች አይደለችም፡፡ ያ ለእኔ ለመቀበል በጣም ቀላል አደረገልኝ፡፡

ከስር ባሉት ማስፈንጠሪያዎች ኦንላይን ማንበብ ወይም ማውረድ ትችላላችሁ።

Leave a Reply