መልካም የእናት ቀን

የእናቶችን ቀን ስናከብር የመንታ እናት የሆነች ኢትዮጵያዊ ሌዝቢያን ለንስንስ የፃፈውችውን ጽሑፍ እናስታውሳለን። ራሷን በመቀበል ሂደት ዙሪያ በፃፈችው ፁሁፍ ላይ ሰዎችን መቀበል የሚችሉና ከሆሞፎቢያ ነፃ የሆኑ ልጆችን የማሳደግ ተስፋዋን ገልጻለች ።

“እንግዲህ የወደፊቱን በተመለከተ ማድረግ የምፈልገው ልጆቼ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ያላቸው አመለካከት እንዳይኖራቸው ማስተማርና በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በሚገባ የተረዳ አስተያየት እንዲኖራቸው መርዳት ነው” ስትል ጽፋለች። 

ዛሬ ለእሷንም ሆነ በህብረተሰባችን ውስጥ ያሉ እናቶችን በሙሉ፣ መልካም የእናት ቀን እንመኛለን።

Leave a Reply