አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ: ኩዊር ለምን ሆንሽ?

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

ከዚህ በታች በአንድ አጋር እና በአንዲት  ኩዊር  ሴት መካከል ስለ ሃይማኖት እና ኩዊር የመሆኗ “ምክንያት” ምን እንደሆነ ከተደረገ ውይይት የተወሰደ ነው።

ኤ- ታዲያ የምርጫ ጉዳይ ነበር? የተወለድሽው በዚህ መንገድ ነው ወይስ ያደግሽበት መንገድ በወሲባዊ ዝንባሌሽ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ይመስልሻል? … እና እንዴት ነው ያደግሽው?

ቢ-  እኔም ከአንተ ጋር እስማማለሁ። ምንም የሚያሳስብ ጉዳይ አይመስለኝም። ሰዎች የተቃራኒ ፆታ አፍቃሪ ለመሆን ይመርጡ እንደሆነ ፈጽሞ አንጠይቅም ፣ አይደል? ታዲያ ኩዊር ሲሆኑ ለምን ምክንያት መፈለግ ያስፈልጋል? የሰው ልጅ የጾታ ስሜት ከጌይ እስከ ባይ እስከ ፓን  ድረስ ያሉትን ሰዎች ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት የወሲብ ዝንባሌ ስሜት ይጨምራል። ሊያሳስበን የሚገባው ይህ ሁሉ የሚከናወነው በፍቃደኝነት እና እድሜያቸው በደረሰ ሰዎች መካከል መሆኑ ነው። 

ያደግኩት ሩኅሩኅ ፣ ደግና አክብሮት ያለው ሰው መሆን እንዳለብኝ ከሚያስተምረኝ የሚወደኝ ቤተሰብ ነበር ። ስለ ደግ እና ሩኅሩኅ አምላክ እንጂ ስለፈራጅ እና ጨካኝ አምላክ ተምረን አናውቅም። እንዲሁም ሁላችንንም እንድንጠይቅና ራሳችን እንድናስብ ያበረታቱን ነበር።  

ኤ- አዎ በጭራሽ ለውጥ ሊያመጣ አይገባም። ግን ያው እንደዛ ነው። 

ቢ- እርግጥ ነው።

Leave a Reply