ከፍቅረኛችሁ ጋር ግዜ እንዴት ታሳልፋላችሁ?

ያለንበት ሃገር የእኛን ማንነት ስለማይቀበል፣ ደህንነትን ለመጠበቅ ሲባል ብዙ ጊዜ ከፍቅር አጋር ጋር ቤት ውስጥ ማሳለፍ እናዘወትራለን። ደህንነትን በጠበቀ መልኩ ምን አይነት ዴት ማሳለፍ እንችላለን? ቤት ውስጥ ብቻ በማዘውተር ስልቹነት እንዳይመጣ ምን ማድረግ እንችላለን? እርግጥ በቤት ውስጥ ምግብ አብሮ ለመስራት መሞከር፣ ስፖርት መስራት፣ ፊልም ማየት፣ ሙዚቃ ማዳመጥ አንዳንዴም የቀን ህልምን አብሮ ማጣጣም ይቻላል። ነገር ግን ከቤት ውጪስ ምን ማድረግ እንችላለን? አንዳንዴ ለመውጣት እናስብና ውጪ ያለውን ጥላቻ ስናስብ ያስጠላናል:: ነጠል ብለን ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

እኔ እና የፍቅር አጋሬ ስልቹነት እንዳይመጣ እነዚህን ነገሮች እያቀያየርን ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ እንሞክራለን።

  • በአቅራቢያ ያለ ቦታ የእግር ጉዞን ማድረግ እናዘወትራለን
  • እንደየምርጫችን የስነጥበብ ፕሮግራሞችን ወይም ቲያትር እንገባለን
  • ግርግር ያልበዛባቸው እና ብዙም ሰው የማያውቃቸውን ሬስቶራንቶች እያሰስን እንከሰታለን
  • ካለንበት አካባቢ እንደየአቅማችን የተለያዩ የመጓጓዣ መንገዶችን እየተጠቀምን ከአአ ወጣ ብለን እንመለሳለን

እናንተስ እንዴት ታሳልፋላችሁ?

ፍቅር ከጥረት ጋር ሲሆን ይበልጥ ይጣፍጣል።

Leave a Reply