በምስራቅ አፍሪካ ዛሬ የጨለማ ቀን ነው። የኡጋንዳ ቤተሰባችንን የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የፀረ ጌ ህግን በመፈረም ወደ ተኩስ ቡድን ወርውሯቸዋል።
እንደ የኡጋንዳ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ አኒታ አንዲ ያሉ አንዳንዶች ህጉን በመፈረም ፕሬዚዳንቱ “የሕዝባችንን ለቅሶ መልሰናል” በማለት ደስታቸውን እየገለጹ ነው። መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶቻቸውን ከማስጠበቅ ይልቅ ሰለባ በማድረግ አገራቸው ለወደቀቻቸው ኩዊር ወገኖቻችን እናለቅሳለን። ማንነታቸውን የመምረጥ መሰረታዊ ሰብአዊ መብታቸውን ተዘርፈዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ የኩዊር ድርጅት እንደመሆናችን መጠን በኡጋንዳ ከሚገኙ ወገኖቻችን አድሎና ጭቆና እየደረሰባቸው ካሉ ወገኖቻችን ጋር በጋራ እንቆማለን። በቅርቡ በኡጋንዳ ፓርላማ የፀደቀው ፀረ-LGBTQIA+ ህግ በLGBTQIA+ ግለሰቦች መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው፤ እናም በጥብቅ እናወግዛለን።
ህጉ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ወንጀል የሚያደርግ ሲሆን ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ ሰዎች ላይ የእድሜ ልክ እስራትን ጨምሮ ከባድ ቅጣቶችን ያስቀምጣል። ይህ በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ መሰርት እና በሁሉም መንግስታት ሊከበር የሚገባውን የግላዊነት፣ የእኩልነት እና አለማዳላት መብትን በግልፅ መጣስ ነው።
በኡጋንዳ ያሉ የLGBTQIA+ ማህበረሰብ ወገኖቻችን እየተሰማቸው ያለው ፍርሃት እና ጭንቀት ይገባናል። የዚህ ህግ መፅደቅ የግለሰብ ነፃነታቸውን ብቻ ሳይሆን ክብራቸውንና ሰብአዊነታቸውን የሚጋፋ ነው። በኡጋንዳ ላሉ LGBTQIA+ ማህበረሰብ ወገኖቻችን ብቻቸውን እንዳልሆኑ ልናረጋግጥላቸው እንፈልጋለን። ለፍትህ እና ለእኩልነት በሚያደርጉት ትግል ከጎናቸው ቆመን ለመብታቸው መሟገታችንን እና ድምፃቸውን ማሰማት እንቀጥላለን።
የኡጋንዳ መንግስት ይህንን አድሎአዊ ህግ እንዲሰርዝ እና የ LGBTQIA+ ግለሰቦችን ጨምሮ የዜጎቹን ሰብአዊ መብቶች እንዲያከብር እንጠይቃለን። አለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህንን ህግ በመቃወም የዩጋንዳ መንግስት በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ ላይ ያለውን ግዴታ እንዲወጣ ጫና እንድታደርጉም እናሳስባለን።
ለLGBTQIA+ እኩልነት የሚደረግ ትግል ለፍትህ፣ ለክብር እና ለመከባበር የሚደረግ መሰረታዊ ትግል ነው። በኡጋንዳ እና በአለም ዙሪያ ካሉ የLGBTQIA+ማህበረሰብ ወገኖቻችን ጋር በመተባበር ፤ ሁሉም ግለሰቦች የመረጡትን የመውደድ እንዲሁም አድልዎ እና ስደትን ሳይፈሩ የሚኖሩበትን አለም መፍጠር አለብን።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላሉ የLGBTQIA+ ማህበረሰባችን አብረናችሁ መሆናችንን ልናስታውሳችሁ እንውዳለን፤ እናንተም በክብር እና በእኩልነት የመኖር መብት ይገባችኀል። በኡጋንዳ ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ቢሆንም፣ እኛም ነቅተን መጠበቅ አለብን እና በሀገራችን ለLGBTQIA+ መብቶች መሟገታችንን መቀጠል አለብን።
በኡጋንዳ ላሉ የLGBTQIA+ ማህበረሰባችን አጋርነታችን እና ለፍትህ እና ለእኩልነት ትግላቸው ያለንን ድጋፍ በድጋሚ መግለጽ እንፈልጋለን። የኡጋንዳ መንግስት ይህንን አድሎአዊ ህግ እንዲሰርዝ እና የ LGBTQIA+ ግለሰቦችን ጨምሮ የዜጎቹን ሰብአዊ መብቶች እንዲያከብር እንጠይቃለን። በጋራ፣ ሁሉም ግለሰቦች ማንነታቸውን የሚያሳዩበት፣ የመረጡትን የሚወዱበት እና አድልዎ እና ስደትን ሳይፈሩ የሚኖሩበት አለምን መፍጠር እንችላለን።