አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ:- የፀረ-ኩዊር ዓመፅን ማስታወስ

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

ከዚህ በታች ያለው በኢትዮጵያ ውስጥ ኩዊር መሆን ሊያስከትላቸው ስለሚችላቸው አደጋዎች ከተደረገ ሰፊ ውይይት የተቀነጨበ ነው።

“የቅርብ ጓደኛዬ የሆነውን ነገር አስታውሳለሁ። ገና ስምንተኛ ክፍል  እያለን ነበር ጌይ መሆኑ የታወቀው፤ ጌይ እንደሆነ  ሲታወቅ ምን ያህል ተቃውሞ እንደገጠመው አስታውሳለሁ። ሁልጊዜ ይደበድቡት ነበር፣ ወደ ምሳና ወደ ሌሎች ቦታዎች ትምህርት ቤት ውስጥ በእግሩ ሲሄድ ትልልቆቹ ልጆች ይደበድቡት ነበር። ይሄ በመሆኑም ትምህርት ቤት መቀየር ነበረበት። ከዚያም የቀየረበት ትምህርት ቤት ያሉ ሰዎችን አግኝተው  ጌይ እንደሆነ ለመናገር ይሞክሩ ነበር። ግን እዛ ትምህርት ቤት ያሉ ሰዎችም ሳይውቁበት ተመረቀ። አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ እየኖረ ነው። አገሩ መኖር አለመቻሉ በጣም  የሚያዛዝን  ነገር ነው። የሚኖርበት ቦታ ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን አሁን አሪፍ ሕይወቱን እየኖረ ነው። ሊያገባም ነው። በጣም ደስ የሚል ነው። ይሄ ከሆነ ጊዜው ረጅም ቢሆንም አሁን ድረስ አስታውሳለሁ ። ምንም እንኳ  የእኔ  [ኩዊርነት] ባይታወቅም ፤ ብገኝ ኖሮ  ምን ሊያደርጉኝ እንደሚችሉ አውቃለሁ።”

Leave a Reply