የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን: የLGBTQ+ የአዕምሮ ደህንነት መደገፍ

መስከረም 30 የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ነው። ለሁሉም ግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአዕምሮ ደህንነት ለሁሉም ማጎልበቻ ጊዜ ነው። ይህንን ቀን ስናስታውስ በLGBTQ+ ማህበረሰብ ዙሪያ ላይ ያለ የአዕምሮ ጤና ላይ ትኩረት እንስጥ። 

የLGBTQ+ ግለሰቦች በአዕምሮ ደህንነታቸው ላይ የተለየ ፈታኝ ሁኔታዎች ይገጥማቸዋል። ከህብረተሰብ አድልዎ እና መገለል እስከ ራስን የመቀበል ትግል፤ ለዚህም ሁሉም ሰው የሚያድግበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ወሳኝ ነው። 

በዚህ የአለም አቀፍ የአዕምሮ ጤና ቀን በአንድ በመሆን ለLGBTQ+ አዕምሮ ጤና ጠንካራ ድጋፋችንን እናሳይ። ከኩዊር ማህበረሰብ ጋር በመገናኘት ደህንነታቸውን እጠይቅ፣ ለማዳመጥ ዝግጁነታችንን እናሳይ፣ ብቻቸውን አለመሆናቸውን እናስታውሳቸው።  እርስ በእርስ መረዳት፣ ርህራሄ እና የመቋቋም ችሎታ እናሳድግ። 

እርዳታ መፈለግ የጥንካሬ መገለጫ መሆኑን እናስታውስ። እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ድጋፍ ካስፈለጎት ለመስማት ዝግጁ የሆነን ሰው ከመጠየቅ ወደኋላ አይበሉ። በጋራ በመሆን ዝምታን እና አድልዎን መስበር እንችላለን፤ የአዕምሮ ደህንነትንም ልናዳብር እንችላለን።

የአለም አቀፍ የአዕምሮ ጤና ቀንን በማክብር ይቀላቀሉን። በማህበረሰባችን ውስጥ ድጋፍ የሚሰጥ፣ የሚያረጋግጥ እና ለLGBTQ+ አዕምሮ ጤና ቅድሚያ የሚሰጥ ባህልን እንገንባ።

Leave a Reply