የኤሴክሽዋል ማንነትን መቀበል እና ደስታን ማግኘት

የኤሴክሽዋል ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት እንደመገባደዱ የኤሴክሽዋል ማንነታቸውን በድብቅ ለያዙ፣ ተናግረውም መረዳትን ላላገኙ እንዲሁም ራስን ለመገንዘብ ጉዞን ለጀመሩ ሁሉ ይህንን ልናስታውሳቸው ወደድን።

ኤሴክሽዋልነትን መረዳት እና መቀበል በሌለበት ሃገር ውስጥ እንደሚኖር ኤሴክሽዋል ሰው ራስ ጋር ድጋፍ፣ መፅናናትን እና ኩራትን መፈለግ ወሳኝ ነው:: የኤሴክሽዋል ማንነትዎን ማዳመጥ ራስን የመፈለግ፣ ራስን የመቀበል እና የራስ እድገትን የሚጠቅም አበረታች ጉዞ ነው።

የምንኖረው በተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪያን ጠል ሃገር ላይ ቢሆንም ብቻዎትን አለመሆኖን ያስታውሱ። መረዳትን እና መልካም ግንኙነቶችን ከኦንላይን ማህበረሰብ ወይም የእናንተን ኤሴክሽዋል ማንነት ከሚያከብሩ ታማኝ ጓደኞች ለማግኘት ይሞክሩ:: ከሚደግፉ እና ማንነቶን ከሚቀበሉ ሰዎች ጋር ማዘውተር ትልቅ ለውጥን ያመጣል።

የስነልቦናዊ ጤናዎን ያስቀድሙ እንዲሁም ራስዎን ይንከባከከቡ:: ለራስዎ በሚያዝናና እና በሚያስደስትዎ ነገር ያሳልፉ፤ የአዕምሮ እና ስነልቦናዊ ጤናዎን መጠበቅ ራስን የመውደስ ተግባር መሆኑን ያስታውሱ።

ምንም እንኳን ምቹ ቦታን እና ደጋፊዎችን ማግኘት አዳጋች ቢሆንም ትንንሽ ግንኙነቶች ራሱ የማህበረሰብ አባልነት እና ተቀባይ ማግኘትን ስሜት ይሰጣሉ:: በኤሴክሽዋል ማንነትዎ ኮርተው የስሜትዎን ትክክለኛነት እና ውበት ያክብሩ:: በማህበረሰባዊ ችግሮች ፊት ልዩ ማንነትዎን ተቀብለው በራስ መቀበል ደስታን ያጣጥሙ።

ማንነትዎ ትክክለኛ እንደሆነ፣ እንዲሁ እንዳሉ ፍቅር እና መቀበል የሚገባዎ እንደሆኑ ያስታውሱ። ራስን በመፈለግ እና በመጎልበት ውስጥ ብርሃኖ ይብራ።

ያስፈልጋሉ! ማንነትዎ ልክ ነው! አይዞኝ!

Leave a Reply