የትራንስጀንደር ግንዛቤ የማስጨበጫ ሳምንት: ቃላቶች እና አበረታች የግል ታሪኮች

የትራንስጀንደር ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ስለትራንስጀንደር የኑሮ ተሞክሮ የምንማማርበት እና ግንዛቤን የምንፈጥርበት ወቅት ነው። በዚህ ፅሁፍ በትራንስጀንደር ማንነት ጋር በተያያዘ አስፍላጊ እና ማወቅ የሚገቡንን አንዳንድ ቃላቶች እንዲሁም የትራንስ ጀንደርን ብርታት እና ጥንካሬ የሚያሳዩ የግል ታሪኮችን እንዳስሳለን። የእነዚህን ቃላቶች ትርጓሜያቸውን እና የተለያዩ የትራንስ ኑሮ ተሞክሮዎችን በማክበር አካታች የሆነን ማህበረሰብ መፍጠር ላይ አስተዋፅዖ እናደርጋለን። 

የትራንስጀንደር ቃላቶች እና ፍቺዎቻቸውን መረዳት: 

ትራንስጀንደር: ትራንስጀንደር ሰዎች የስርዓተ ፃታ (gender) ማንነታቸው በውልደት ያገኙት ፃታቸው (sex) ጋር ሳይመሳሰል ሲቀር ማለት ነው:: በወንድ፣ ሴት ወይም ከሁለትዮሽ ፃታ ያልሆነ (non binary) ፃታ የሚገለፁ ሊሆኑ ይችላሉ፤ የህይወት ጉዟቸውም እውነተኛ ማንነትን መቀበል ይገኝበታል። 

ሲስጀንደር: ሲስጀንደር ሰዎች ስርዕተ ፃታቸው ከውልደት ፆታቸው ጋር ሲመሳሰል ማለት ነው። ለምሳሌ : አንድ ሰው በውልደት ፃታ ሴት ቢሆንና ስርዓተ ፃታ በሴት ቢገለፅ ሲስጀንደር ነው ማለት ነው።

ከሁለትዮሽ ፃታ ያልሆኑ (Non binary): ከሁለትዮሽ ፃታ ያልሆኑ ሰዎች በሴት ወይም በወንድ መደብ ለይተው አይገለፁም። በሁለቱም ሊገለፁ ይችላሉ ወይም በየትኛውም ወይም ደግሞ በሌላ ስርዓተ ፃታ። ከሁለትዮሽ ፃታ ያልሆኑ ሰዎች ባህላዊውን የስርዓተ ፃታ ሃሳብ በመሞገት ሰፋ ያለ ማንነቶችን ይቀበላሉ።

ጀንደር ዲስፎርያ: ጀንደር ዲስፎርያ አንዳንድ ሰዎች የውልደት ፃታቸው እና ስርዓተ ፃታቸው ሳይገናኝ ሲቀር የሚፈጠርባቸው ምቾት የመንሳት እና የጭንቀት ስሜትን ይገልፃል። የጀንደር ዲስፎርያን ውይይት ወይም ገጥመኝ ሲኖር በማስተዋል እና በቅንነት መያዝ ያስፈልጋል። 

በሰፊው ማህበረሰብ የትራንስጀንደር ጠልነትን መኖር ማወቅ እና በተቻለን መቃወም እጅግ አስፈላጊ ነው፤ በእኛው ኩዊር ማህበረሰብም እንዲሁ።

አበረታች ታሪኮች: 

ከማህደራችን የተቀነጨቡ ሁለት ታሪኮችን እናካፍላችሁ። የትራንስጀንደር ሰዎችን የግል ታሪክ እያካፈልን ድፍረት እና ድሎቻቸውን ማክበር እንዳለብን እናምናለን።

ዋሂራ ላቤል  

ዋሂራ ላቤልን እናስተዋውቃችሁ። አሁን ላይ በአሜሪካ የምትኖረው አብዮታዊት የምስራቅ አፍሪካ እህታችን ራሷን ለመቀበል ባደረገችው ጉዞ ብዙ መሰናክሎችን ተጋፍጣለች። ጭፍን ጥላቻ እና መድልዎ ቢገጥማትም የራሷን እውነት ይዛ አሁን የትራንስጀንደር መብት ተሟጋች በመሆን ብዙዎችንም እያነሳሳች ትገኛለች። 

ራስን የማወቅ ጉዞሽ ምን ይመስል ነበር?

አክራሪ የእስልምና ተከታይ በሆነችው ትንሽዬ የሶማሊ መንደው ውስጥ ባድግም ገና በልጅነቴ የተለየሁ እንደሆንኩ አውቄ ነበር። ከብዙ ውስብስብ ስሜቶችና ራስን የማወቅ ፍላጎት በኋላ ወደ ኬንያ ስደተኞች ካምፕ ለመግባት ወሰንኩ። እዛም ብቻዬን እንዳልሆንኩ አወኩ። እንደኔ በአለም ላይ ሌሎች ትራንስ ሰዎች እንዳሉ በማወቄ የኔ ልዩነት ተጨባጭ እንደሆነ እና የሌሎችም እውነታ እንደሆነ፣ ልረዳው እና ላከብረው እንደምችል ገባኝ:: ያኔ ነው ራሴን የተቀበልኩት ምንም እንኳን የተለየ ማንነት ስጋት ቢኖረውም።

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን እዚህ ማንበብ ይችላሉ

ሜላት እና ሩት 

ሜላት እና ሩት ራሳቸውን ከሁለትዮሹ ስርዓተ ፃታ ውጪ የሚገልፁ ሁለት ኢትዮጵያውያን ናቸው:: የህይወት ተሞክሮዎቻቸውን በኢትዮኩዊር ፖድካስት በኩል አካፍለውናል:: ይህ ውይይት ሰዎች ርሳቸውን የሚሰይሙባቸውን እና የሚገልፁባቸውን የተለያዩ የስርዓተ ፃታ መንገዶች ላይ ግንዛቤን ይሰጠናል፤ በዚሁ ዙሪያ ቋንቋ እና ባህል ያለውንም ውስስንነት የተሻለ እንድንረዳ ይጠቅመናል:: 

ፖድካስቱን እዚህ ማዳመጥ ይችላሉ። 

የትራንስጀንደር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ስለትራስንጀንደር የምንማማርበር፣ የትራንስ ማህበረሰብን የምንረዳበት እና የምናከብርበት ጊዜ ነው። ከላይ የተቀመጡትን ቃላቶች በመረዳት እና የተለያዩ ግላዊ ታሪኮችን በመቀበል ከላይ እንደገለጥነው የበለጠ አካታች ማህበረሰብን መፍጠር ላይ መሳተፍ እንችላለን። እንዲሁም በሰፊው ማህበረሰብ የትራንስጀንደር ጠልነትን መኖር ማወቅ እና በተቻለን መቃወም እጅግ አስፈላጊ ነው፤ በእኛው ኩዊር ማህበረሰብም እንዲሁ። ግንዛቤን እየፈጠርን እና እያስተማርን ትራንስጀንደር ሰዎችን የሚያከብር እና የሚደግፍ ሁሉን አካታች የሆነ አካባቢን ለመፍጠር በጋራ እንስራ። በጋራ አድልዎን በመቃወም ሁሉም ሰው በእውነት፣ በሰላም እና በክብር መኖር የሚችልበትን የወደፊት ጊዜ መፍጠር እንችላለን።

Leave a Reply