በደስታ እና በፍርሃት ድብልቅልቅ ባለስሜት በምናቤ የደነስኩ ነበር። የማወቅ ጉጉት ነበረኝ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሌሎች ኩዊር ሰዎችን ለማግኘት በጣም ጓጉቻለሁ። በዚያን ጊዜ፣ “ማህበረሰብን መፍጠር” ለማለት ቃላት አልነበሩኝም፣ ነገር ግን እንደ እኔ ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር መሆን የማይካድ ፍላጎቴ ነበር። ሶስት ነበርን እና እኔ ብቻ ነበርኩኝ በኢትዮጵያ የኩዊር ስብስብ ሆነ ፖርቲ ላይ ተገኝቼ የማላውቀው። ልቤ ኩዊሮች ባሉበት ለመገኘት በጉጉት ሮጠ፣ነገር ግን በውስጤ የጭንቀት ቋጠሮም ተሰማኝ፤ ነገሩማ በሀገራችን ኩዊር መሆን ህገወጥ ነው።

ወደ ስፍራው እየሄድን፣ የጉጉት እና የፍርሃት ድብልቅልቅ ስሜት ተሰማኝ። በቦታው ስንደርስ ውጭ ላይ ቆመን የጋበዘንን ሰው ደውለን ወደውስጥ እንዲያስገባን ነገርነው። ምን እንደሚጠብቀን ምንም ፍንጭ አልነበረኝም። በሩ ሲከፈት ግን ሞቅ ያለና ደስ የሚል ድባብ ውስጥ ገባን። ጥቂት ሰዎች በቡድን ሆነው እየተጨዋወቱ እና እየሳቁ ነበር እውነት አልመስል አለኝ። መጠጥ እና ውሃ እየያዝን ቤቱን አልፈን ወደውስጥ ስንገባ፣ በግድግዳው ላይ እንደ አበባ እየተሰማኝ ፣ ራሴን ተደንቄ፣ ተገርሜ እና በተለያየ ስሜት ውስጥ ሆኜ አገኘሁት። ምሽቱ ገና ልጅ ነበር። ነገር ግን ከ 10 እና 15 በላይ ሰዎች እንደማይመጡ አስበን ነበር።
ከ30 ደቂቃ በኋላ አየር ለማግኘት ወደ ውጭ ለመውጣት ወሰንን። ብዙ ሰዎች እዚያ ተሰብስበው ማየት እንዴት ድንቅ ነበር! አብዛኞቹ የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ወንዶች ነበሩ፣ ከጥቂት ሴት አጋሮች ጋር ተደባልቀው። ከስራ የማውቀውን ሰው ራሱ እዛ መሃል አየሁት! ብዙ ኩዊር ሰዎች ማየት በጣም ደስ የሚል ነበር፣ ነገር ግን ብዙ ሴቶች ቢኖሩ ብዬ መመኘቴ አልቀረም።
ከዚያ ምሽት ጀምሮ፣ ለሴቶች ብቻ የተወሰኑትን ጨምሮ ብዙ የኩዊር ፕሮግራሞችን ተካፍያለሁ። እያንዳንዱ ተሞክሮ ልዩ እና መንፈስን የሚያድስ ነበር፣ ግን ያንን የመጀመሪያዬን ሁልጊዜ አስታውሳለሁ። ብዙ ጊዜ ማንነታችንን መደበቅ ባለብን ዓለም ውስጥ ለመሰባሰብ እና ለመገናኘት ስጋት ወስደን መገኘታችን ለሁላችንም የጀግንነት ውሳኔ ነው። እንደትንሽ አብዮት ተሰምቶኝ ነበር፣ እናም በዚህ ውስጥ በመገኘቴ ትልቅ ምስጋና አለኝ።