
በቲክቶክ ብዙ ተከታዮችን ያፈራው የ33 አመቱ ናይጄሪያዊ ክሮስድሬሰር ኤርያ ማማ በትላንትናው እለት መገደሉን ተከታዮቹ እና የናይጄሪያ ዜና ዘግባል።
እንደናይጄሪያ ያሉ አፍሪካ ሃገራት LGBTQ+ የሆኑ ሰዎች በተለያየ ጊዜ ብዙ አይነት ጥቃት እና መገለል ይደርስባቸዋል:: በእነዚህ ሃገራት የኤልጂቢቲኪው+ ማንነቶች እንደወንጀል ቢቆጠሩም እን ኤርያ ማማ ያሉ ሁሉ የሃገሪቱ ዜጎች ስለሆኑ ብቻ የህግ ከለላ እና ፍትህ ይገባቸዋል። ከጥቂት ጊዜያት በፊት ኤርያም ጥቃት ደርሶብኛል ብሎ በቲክቶክ ገፁ እስከእነቁስሉ ቀርቦ ያለውን ሁኔታ ቢዘግብም የህግ ከለላን እና ፍትህን ሳያገኝ ቀርቷል።
የኤሪያ ቲክቶክ አዝናን ብቻ ሳይሆኑ አስተማሪ ነበሩ። ለናይጄሪያውያን እና ለመላው አፍሪካውያን ክሮስድሬሰርስ የመታወቅን መድረክ በመክፈት ብዙ ድጋፍን አበርክቷል።
ለኤርያ ቤተሰብ፣ ጏደኞች እና ደጋፊዎች ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን:: ጀግንነቱ እና ለLGBTQ+ መብት ያበረከተው አስተዋፅዖ ሁሉ መቼም አይረሳም።
ትግሉ ይቀጥላል!
