Skip to content Skip to footer

አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ:- የህብረተሰቡን የሴትነት “ግዴታዎች” መፈተሽ

ከስር ያቀረብንላችሁ  <<አጫጭር ታሪኮች ከግል ማስታወሻ ላይ>> ከኩዊር ማህበረሰብ በፍቃድ ከሚላኩልን የግል መልእክቶች፣ የግል ማስታወሻዎች እንዲሁም ግለ ታሪኮች ላይ እየቀነጫጨብን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። እነዚህ የፅሁፍ ቅንጭብጫቢዎች ልክ ህይወታችን አስልተን እንደማንኖራት ሁሉ የቆምንበትን የህይወታችንን ትክክለኛ ገፅ  የሚያመላክቱ  አንዳንዴ መግቢያ፣ ሌላ ግዜ ተሟልተው ያልተፃፉ እንዲሁም የተዘበራረቁ ፅሁፎች ናቸው።

 ይሄን ፅሁፍ ከምታነቡ ማንኛችሁም የኩዊር ቤተሰቦች የእናንተንም ማስታወሻ እንደምንቀበል በደስታ እያሳወቅን በetqueerfamily@gmail.com ኢሜይል እንድትልኩልን እንጠይቃለን። .

ከዚህ በታች ያለው በኢትዮጵያ ውስጥ ህብረተሰቡ የሴትነት ግዴታዎች ብሎ የሚያስባቸውን ነገሮች አንድ “ወንዳወንድ” ኩዊር ሴት እንዴት እንደምትፈትሻቸው ከተደረገ ውይይት የተወሰደ ነው።

በአብዛኛው ችላ እላቸዋለሁ። በርግጥ ይህ ከልዩ መብት እንደሚመጣ እገነዘባለሁ። ከፍቅር ጓደኛዬ ጋር ስንሆን እና እንደ ሌዝቢያን በቀላሉ እንደምታይ ስለምገምት የሚያሳስበኝ ጊዜ አለ። እሷን ለአደጋ እያጋለጥኩ ነው በሚል እሳቤ ሰዎች ሊያጠቁን እንደሚችሉ እያሰብኩኝ እጨነቃለሁ። እራሴን በመሆን ይመስለኛል ይህን ነገር የማሸንፈው። ቤተሰቦቼ የፆታ አገላለፄን በጣም ይቀበላሉ፤ በምንም መልኩ እንድቀይረው አይጫኑኝም። ለእኔ የደህንነቴ መሰረት ናቸው። ለኔ የቆሙ መሆናቸውም ሰፊውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እንድጋፈጥ ብርታት ይሰጠኛል። እንደ “ከቤ” ያሉ ቃላትን አልወድም እናም ሰዎች እንደዚህ አይነት ቃላትን ሲጠቀሙ እናገራለሁ። አለመፍራት እና እውነትን ብቻ መኖርን ተምሬያለሁ። ይህ ማለት አላስፈላጊ ሁኔታዎች ውስጥ እገባለሁ ማለት አይደለም። ነገር ግን የበለጠ ሃሳቤን የምገልፀበት ሁኔታ ላይ ደርሻለሁ።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading