Skip to content Skip to footer

ኢትዮኩዊር ፖድካስት: በኩዊር ማህበረሰብ ውስጥ አግባብ ያልሆኑ ባህሪያትን ስለመፈተሽ

“Lately በጣም ያስቸገረኝ ነገር stalking.. በተለያየ ቁጥር… በተለይየ አካውንት..ይሄ መጥቼ ለቤተሰቦችሽ እናገራለሁ ምናምን የተለመደ ነገር ነው” ትላለች በእኛ ማህበረሰብ ስለሚፈጠሩ አግባብ ያልሆኑ ወይም መርዛማ ባህሪያት ስታብራራ “ያንቺ nude picture ስላለኝ የማደርግሽን እኔ አውቃለሁ ችግር የለውም..” ካጋጠማት እያጣቀሰች ትወያያለች። የስርዓተ ፃታዋ አገላለፅ ምን ነበር ለሚለው የእርስ በእርስ ጥያቄ  [ቡች ላይ ብቻ ነው ብዙ ጊዜ Toxicity አለ የሚባለው ግን ለኔ Toxicity እንደባህሪይ የሚንፀባረቅ ነገር ነው እንጂ አቋም አይደለም] ትላለች ሌላኛዋ እንግዳችን…

ተጋባዥ እንግዶቻችን አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን በማንሳት እርስ በእርስም በጥሩ ሙግት በመያያዝ ስለሃሜት፣ ያላግባብ ክትትል፣ ቁጥጥር አለመከባበር ፣ ስርዓተ ፃታ ጥቃት እና ሌሎችም በጥልቅ አወያይተውናል። ታዲያ ጉድለቶቻችንን ብቻ ተወያይተን አልተለያየንም፤  እንዴት የተሻለ ማህበረሰብን መፍጠር እንደምንችልም መልካም ሃሳቦችን ሰንዝረው የቤት ስራ ሰጥተውናል። 

የሶስተኛው ክፍል የመጀመሪያውን ውይይት እዚህ ላይ ማዳመጥ ይችላሉ።

በኢትዮኩዊር ፖድካስት ላይ ታሪኮቻችሁን ማጋራት የምትፈልጉ ወይም ሃሳባችሁን መስጠት የምትፈልጉ ሁሉ በ etqueerfamily@gmail.com ልትፅፉልን ትችላላችሁ።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading