የፍቅረኛሞች ቀንም የአበባም አድናቂ አይደለሁም:: ምንም እንኳን የፍቅረኛሞች ቀን ካፒታሊስት እና ተቃራኒ ፃታ አፍቃሪነትን ብቻ ልክነትን የሚስል ባህል ነው ብዬ ብከራከርም፥ ጓደኛዬ ለፍቅረኛዋ አበባ እንዳደርስላት ጠየቀችኝ::
በተላላኪዎች መላክ አልቻለችም ምክንያቱም ሴት ለሴት ቀይ አበባ መላክ አዲስ አበባ ላይ የቀስተ ደመና ባንዲራ እንደማውለብለብ ነው::
ምንም እንኳን ጓደኛዬ በገዛችልኝ ምሳ ብደሰትም፤ እንዲህ አይነቱን ፍቅር ለመገላለፅ ድብብቆሹ እና ፍርሃቱ አሳዝኖኛል:: ይሄ ሁኔታ ለኩዊር ሰዎች ፍቅር በብዙ መንገዶች በህይወታችን እንዳለ እንዳስታውስ አድርጎኛል:: ከዚህ በታች ያሉት አባባሎች ፍቅር እንደሚፀና በኩዊር ሰዎች እና ደጋፊዎች የተፃፉ ጥሩ ማስታወሻዎች ናቸው::

“ፍቅር ፆታ የለውም፣ ርህራሄ ሃይማኖት የለውም ፤ ባህሪይ ዘር የለውም::” – አብሂጃት ናስካር
“ፍቅር በፍፁም በፍርሃት መኖር ማለት የለበትም::” – ዳሻኔ ስትሮክስ
“ሌዝቢያን መሆን ማለት ያልተለመደን መውደድ እድል ማለት ነው፤ በዚህም ግድ የለኝም:: ፍቅር ነው የሚለውን እውነታ ስለተቀበልኩ በምመራው ህይወት ምክንያት አልናደድም፤ አላለቅስም።” – ጄና አን
“የትኛውም መንግስት ዜጎቹ መቼ እና ማንን መውደድ እንዳለባቸው የመናገር መብት የለውም።” – ሪታ ሜ ብራውን
“ለኔ ሴት መውደድ ቦታ ያልነበረው አለም መኖር የምፈልግበት ወይም የምታገልበት አለም አልነበረም::” – ኦድሬ ሎርድ
“የምታፈሪው ስርዓተ ፆታን ሳይሆን ሰውን ነው::” – ሳንድራ አልቫሬንጋ
“መጨረሻውን ቁረጥ:: ፅሁፉን አሻሽል:: የህልሟ ወንድ ሴት ነች::” – ጁሊ አን ፒተርስ
“ለኤለን ያለኝ ስሜት ሌዝቢያን ሆኖ የመውጣትን ፍርሃት አሸንፏል። ከእሷ ጋር መሆን ነበረብኝ፣ እና በኋላ ላይ ሌሎች ነገሮችን እንደማስተናግድ አሰብኩ።” – ፖርሽያ ደ ሮሲ
“እኛ ሌሎች ሰዎች እንደሚሉን አይደለንም። እኛ እራሳችንን መሆን እንደምናውቀው ነን እና እኛ የምንወደው ነን:: ይህ ደግሞ ምንም ችግር የለውም:: ” – ላቬርኒ ኮክስ