ወደ ፕሮግራሙ ቦታ መግባት ለማመን የሚከብድ ስሜት ነበረው ልክ እንደ ዳግም መገናኘት አይነት ስሜት ነበረው። ለዓመታት ያላየኃቸው ሰዎች እና ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ የማውቃቸው መሀል ነበርኩ። እንደ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳግም መገናኘት አይነት ነገር… ሁሉንም በግል ባታውቋቸውም ነገር ግን ታሪኮቻቸውን፣ ደስታቸውን፣ ጉዟቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተከታተላችኋቸው ስለሆነ የምታውቁት ቦታ አይነት ስሜት አለ አይደል?…