የዚህ ወር ፖድካስታችን በአንድ የክልል ከተማ የምትኖረውን ዮርዳኖስን ይዛላችሁ መጥታለች። ዮርዳኖስ በተለምዶ “ወንዳወንድ" የምትባል ሌዝቢያን ናት፥ ስርዐተ ፆታን ለእርሷ ትርጉም በሚሰጥ መልኩ እንደገና በመተርጎም ፥ የስርዐተ ፆታ ማንነቶችንን ወይም የስርዐተ ፆታ አገላለጾችን ዋጋ በማይሰጥ ሀገር ውስጥ መኖር፥ በሰፊው ማህበረሰብ እና በኩዊር ማህበረሰብ ውስጥ እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለባት ትልቅ ትምህርት አስተምሯታል። ካነሳናቸው ሃሳቦች መሃል ጥቂቱን ቀንጨብ አድርገን…