ልጅ እያለው ዘመድ ጥያቄ ነበርኩ። ሩቅ ያሉት ዘመዶቼ ጋር በመሄድ አሳልፍ ነበር። ከሰው ጋር በጣም ተግባቢ የምባልና ከዘመድ አዝማዶች ጋር ጊዜ ማሳለፍ የሚወድ ልጅ ነበር። በጣም ነበር የምወደው! ነገር ግን ወደኩዊር ማንነቴ ስመጣ ይሄ ነው የምለው ነገር እንኳን ባይቀየር ብዙ ነገሮች ተለወጡብኝ። ስለማንነቴ ያፋጠጠኝም፣ የጠየቀኝም አልነበረም። ማናቸውም ክፉ ቃል አልተናገሩኝም። ማናቸውም ፊቴ ላይ በራቸውን አዘጉብኝም።…