የአፍሪካ ቀን በአፍሪካዊያን እና በመላው አለም በሚገኙ አፍሪካውያኖች በሙሉ የሚከበር ቀን ነው። ግንቦት 17 የሚከበረው ይህ የአፍሪካ ቀን የአፍሪካን አንድነት ህብረት ምስረታን አስቦ ይውላል። እኛ አፍሪካውያንም ባለንበት ቦታ ሁሉ ሆነን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህላችንን፣ ታሪካችንን እና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ስኬታችንን አስበን የምንውልበት ቀን ነው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለኢትዮጲያውያኖች ትልቅ ትርጉም አለው። ቀዳማዊ ሃይለስላሴ የአፍሪካ አንድነት ህብረትን…