ለመጀመሪያ ጊዜ ፕራይድ የተካፈልኩት ከሃገር የመውጣት ገጠመኙ ተፈጥሮ ነው፤ ከአንድ አምስት ስድስት አመት በፊት:: አንድ የአውሮፓ ከተማ ላይ በጣም በትልቁ ደምቆ የተከበረበት ቀን የመጀመሪያው ትውስታዬ ነው:: ልክ አዲስ አበባ ላይ እንዳለው እንደታላቁ ሩጫ ዋና ጎዳናዎችን በተለያዩ ሙዚቃ እና ዳንሶች ታጅቦ ኩዊር ማህበረሰብን ማየት እንዴት እንባ አያስመጣ! የደስታ እንባ! ነፃነት ለካ እንደዚህ ደስ ይላል፤ ራስን ሆኖ…