በአንዱ ቀን ማለዳ ከእንቅልፏ ስትነቃ መጀመርያ እኔን ማግኘት እና ማቀፍ ፈልጋለች። እኔም በሀሳብ ረመጥ ተነክሬ ከናፍቆት ዋርካ ስር በመቀመጥ በተስፋ እጠብቃታለሁ። መንቃት አለባት እላለሁ ለራሴ። ግዴታዋ እንደሆነ ነው የማስበው። የጠዋቷ ጮራ ደምቃ በምድር ትከሻ ላይ ብታሸበርቅም ለኔ ግን ገና ነው አልነጋልኝም። የኔ ንጋት እሷ ናትና ። በድንገት ግን የአይኖቿ ቆቦች ተገለጡ።…