ማህበራዊ ሚዲያ ምንም እንኳን ብዙ ጥቅሞች ቢኖሩትም በጥላቻ የተሞሉ ሰዎችን ማየት ደግሞ ሌላው ጎን ነው:: "ጌ እገላለሁ" ከሚለው አንስቶ "የቤተሰቤ አባል ጌ ቢሆን አባርረዋለው" ድረስ የተለያዩ ጥላቻዎችን አይቻለሁ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ስለእኔ ማንነት የቅርብ የምላቸው ጓደኞቼም ይሄንን አይነት መልዕክት ላይክ ሲያደርጉ አይቻለሁ:: አስቡት በጣም የምትቀርቧቸው ጓደኛችሁ እንዲህ አይነቱን ጥላቻ ሲያበረታቱ! ድሮ ድሮ በፍራቻ ዝም እል ነበር::…