የባይሴክሽዋል ማንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንትን ባይሴክሽዋል ሰዎችን በማስታወስ እና በማክበር እናሳልፍ:: ባይሴክሽዋል ሰዎች ባይ ጠልነት የመሳሰሉ ልዩ ተግዳሮቶች ከተቃራኒ ስርዓተ ፃታ አፍቃሪያን እና ኩዊር ማህበረሰብ ይገጥማቸዋል:: ይህ የስዕል መረጃ ጠቃሚ እውነታዎችን ያካፍላል እንዲሁም የመታየት፣ የመረሳት እና የማህበረሰብ ድጋፍ አስፈላጊነትን ያስተምራል። እንደ ማህበረሰብ፣ እነዚህን የተዛባ እና ጅምላ አመለካከቶችን በመቃወም እና የበለጠ ሁሉን አቀፍ እና ንቁ የኩዊር ማህበረሰብ ለመፍጠር እርስበርስ መበረታታት እና መደጋገፍ እንችላለን።
