
እንደኩዊር ኢትዮጵያ ለእናንተ ለተወደዳችሁ የኩዊር ማህበረሰብ አባላት ከልብ የመነጨ የአዲስ ዓመት መልዕክታችንን ማስተላለፍ እንፈልጋለን::
ብዙ ፈተናዎች እና መሰናክሎች ቢኖሩብንም ማንነታችንን ለማክበር እና እርስ በእርስ ለመደጋገፍ ቆራጥነታችን እንደቀጠለ ነው:: ያለፈው ዓመት ብዙ ችግሮችን እና ግርታዎችን ብናስተናግድም የማህበረሰባችንን የሚገርም ፅናትና ጥንካሬም አሳይቶናል:: በህብረት ሆነን ጎን ለጎን በመቆም ሳንታክት ለራሳችን ታግለናል::
አዲሱን ዓመት እርስ በእርስ መደጋገፉን ፣ ታሪኮቻችንን ማካፈሉን እና መፃፉን፣ ልዩነቶቻችንን ማክበሩን እንቀጥል:: እንቅፋቶቻችንን እያስወገድን በLGBTQ+ ማህበረሰባችን ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣትን እንቀጥል::
የዚህ የሚደንቅ ማህበረሰብ አባል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል፤ የሚቀጥሉት ጊዜያት ምን እንድሚመስሉም ለማየት ጓጉተናል::
አዲሱ ዓመት የፍቅር፣ የደስታ እና አብሮነትን የምናጠናክርበት ዓመት ይሁንልን::
መልካም በዓል!