Skip to content Skip to footer

በዓል፡ ቡና፣ ዶሮ ወጥ እና ተስፋ

የዘንድሮ የገና በዓል በጣም በመልካም ሁኔታ ነበር ያለፈው። ለመጀመሪያ ጊዜ እኔና የትዳር አጋሬ ቤተሰቧን በሙሉ በቤታችን ውስጥ አስተናግደናል። ለእነሱ፣ አብረን የምንኖር ሁለት በጣም ጥሩ ጓደኞች ብቻ ነን። እውነቱን ለመናገር ይህ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም፣ ለጊዜው ግን እነዚህን ጊዜያት ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንድናካፍል የሚያስችለን ታሪክ ነው።

እና አስደሳች ጊዜ ነበር። ቡና አፍልተን መዓዛው ከእጣን ሽታ ጋር ክፍሉን ሞላው። እና ዶሮ ወጥ፣ ክትፎ እና በዓልን በዓል የሚደረጉ የኢትዮጵያ ነገሮችን በሙሉ ተጋርተናል። ለእነዚያ ጥቂት ሰዓታት፣ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ እየሳቅን እና እየበላን ጊዜ ማሳለፋችን፣ እንደማንኛውም ቤተሰብ እንደሆንን ተሰማን። ሚስቷ ወይም የትዳር አጋሯ ላይሉኝ ይችላሉ ፡ ነገር ግን እንደ “ምርጥ ጓደኛዋ”፣ አጋር የሚያደርገውን ሁሉ ማድረግ ችያለሁ። ማስተናገድ፣ መንከባከብ፣ ከእሷ ጋር ቤት መገንባት ቻልኩ።

ምሳ ብቻ ሳይሆን፤ ቃላቶቹ ሳይነገሩ ቢቀሩም እንኳን አብረን ለምንኖረው ሕይወት ምስክርነት ነበር።

ተስፋ አለኝ። ምናልባት በጥቂት ዓመታት ውስጥ እንደገና እናስተናግዳቸዋለን። እና በሚቀጥለው ጊዜ፣ ምናልባት ፡ ምናልባት ፡ ልክ እንደ ሌላ ጥንዶቹ በግልጽ የኑሮ አጋሯ እንደሆንኩኝ ታውቆ ይሆናል።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading