Skip to content Skip to footer

ኤክስ፣ ጓደኝነት እና ገደብ

“ከሁሉም ኤክሶችሽ ጋር ጓደኛ ነሽ?” በመተዋወቅ ላይ ያለን ልጅ ጠየቀችኝ። “ምነው አትደግፊውም?” አልኳት ተደናግሬ… እንደማትደግፈው ሳታቅማማ ነገረችኝ።

እናንተስ ምን ትላላችሁ? 

ሁለት የፍቅር ታሪክ የነበራቸው ሰዎች የፍቅር ግንኙነቱን ሲያቋርጡ ሁሉንም አይነት ግንኙት ማቋረጥ አለባቸው ብዬ አላስብም። ይበልጥ ደግሞ ያሳለፉት የፍቅር ጊዜ ክፋት የሌለበት ከሆነ በውይይት ወደተሻለ አማራጭ መግባት ይችላሉ ብዬ አስባለሁ። ይህን ብልም ለጓደኝነት አይደለም ደግሜ ማየት የማልፈልጋቸው ኤክሶች አሉኝ። ነገር ግን ጓደኛ ሆነን መቀጠል የቻልን ደግሞ ፍቅራችን የማንንም መስመር ሳይዘል በመተሳሰብ እየኖርን ነው። አንዳንዴ ከላይ እንደጠቀስኩት ዴት ላይ ጥያቄዎች ይነሱና ለዴቱ መቀጠል እና አለመቀጠል ትልቅ ጥያቄን ይፈጥራሉ። 

ከላይ የጠየቀችኝም ጋር እንዲሁ…. ለየትኛውም አዲስ ፍቅር እና ዴት ከድሮ ፍቅረኞቼ ዛሬ ላይ ደግሞ ምርጥ ጓደኞቼ ጋር ግንኙነቴን ስለማላቆም የእኔ እና የሷ ትውውቅ በአጭር ተቀጨ። 

እናንተስ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?  

እኔ እንደማምነው ከሆነ እወድሻለሁ የምትለኝ ሴት አብራኝ  ለመዝለቅ ምርጫዬን ማክበር አለባት፤ እኔም የሷን ምርጫ እንደዛው። ቅድም እንዳልኩት ታዲያ መስመርን በአግባቡ መጠበቅ ይኖርብናል። የምናሳልፈው ጊዜ፣ የምናወራው ወሬ እና የመሳሰሉት ላይ ገደብ አበጅተን ከፍቅረኛ ጋር ያለውን ነገር በግልፅ በመነጋገር ጓደኝነቱን ማስኬድ ይቻላል።

እናንተስ? ፍቅረኛችሁ ከኤክስ ጋር ጓደኝነት ቢኖራት ምን ይመስላችኋል? ከኤክስ ጋርስ ጓደኛ መሆን ብትፈልጉ ምን አይነት ገደብ ታሰምራላችሁ?

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading