Skip to content Skip to footer

ከቃለ መጠይቅ የተቀነጨበ፡ አዲስ አበባ ውስጥ ያለች ኩዊር ሴት ኩራት

በኢትዮጵያ ውስጥ በኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ አመለካከቶችን ለመዳሰስ ጥረት እናደርጋለን። በአዲስ አበባ ከምትኖር አንዲት ኩዊር ሴት ጋር ስለ ኩራት ትርጉም ተነጋግረናል። ይህም ከዛ የተቀነጨበ ነው።

የእሷ አመለካከት፡፡

ስለኩራት የተለየ ትልቅ ነገር ተሰምቶኝ አያውቅም። ለእኔ፣ እንደ ሰርከስ ነገር ነው የሚሰማኝ፤ ልክ የልደት ቀንዎን በየዓመቱ ማክበር ስለሚጠበቅብዎት ብቻ ማክበር እንደማለት ነው።

እውነተኛ ኩራቴ የተለየ ነው። በማህበረሰቤ ኩራት ይሰማኛል፤ በግሌ የማውቃቸው እና የማገኛቸው ኩዊር ሰዎች ያኮሩኛል። ጠንካራ ማህበረሰብ የገነባን ይመስለኛል። ማህበረሰብ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ከምንም ነገር በላይ የኩዊር ማንነትን የሚፈጥረው ያ ነው።

እነዚህ አስተዋይ ሰዎች ናቸው፣ ሁሌ ከምንም ነገር የሚጠብቁኝ ሰዎች ናቸው። አስፈላጊ እና ትርጉም እንዳለኝ እንዲሰማኝ ያደርጉኛል።

ይህ ነው ኩራቴ።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading