የኩራት ወር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ደጋግመን የምንሰማው ነገር ኩራት እንደኛ ላሉ በጭቆና እና መገለል ውስጥ ለሚኖሩ የLGBTQ+ ማህበረሰብ ትርጉም የለውም” የሚል አስተሳሰብ ነው።
እኛ እዚህ ላይ የተለየ አስተያየት አለን። ኩራታችን በብዙ መንገዶች ይገለጣል። በብዙ መንገድም እየኖርነው ነው። የኩራት ወር እየተገባደደ እንደመምጣቱ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ኩራታችን የተትረፈረፈ፣ የማያልቅ እና ውብ እንደሆነ የምንተዋወስበት ጊዜ ይሆናል ። ኑ! አዎንታዊ እና በሽ ኩራትን ወደምንፈትሽበት እና ወደምናወዛበት ጉዞ ተቀላቀሉን::

“ስለምን ኩራትን እናክብር ያለነው እኮ ጭቆና መሃል ነው?”
ልክ ነው! ጭቆና መሃል ነን:: ነገር ግን ካሰብንበት ትላንትን ስላይደለን ብዙ የምናከብረው አለን::
– ራስን በመቀበል ባለመቀበል ትግልን ስላሸነፍን
– ትግል ውስጥ ብንሆንም ኮሚኒቲ ፍለጋ እዚህ ስላለን እና ጉዞን ስለጀመርን
– ሌሎች ምን ይሉኛልን ሳንፈራ የፈለግነውን ፀጉር ቁርጥ ይሁን አለባበስ መርጠን እየኖርን ስላለን
– ብንፈራም ከትላንት የተሻለ ጥቂትም ቢሆን እየሞከርን ስላለን
– ከራሳችን አልፈን ሌሎችን “ብቻችሁን አይደላችሁም” ማለት ስለቻልን
– እያለፍንበት ያለውን ህይወት ሌሎችን እርዳታ መጠየቅ ስለቻልን
– ፍቅርን መቀበል እና መስጠት መቻላችን
– ነገ ግር ቢልም ዛሬ ላይ ፍቅርን ለመመስረት ጉዞ ስለጀመርን
– ብቸኝነትን መርጠን ህይወትን በምንችለው ሁሉ እየኖርን ስላለን
እያንዳንዱ የህይወታችን እርምጃ ኩራት ነው:: በድብቅ ህይወት ውስጥ ነፃነትን ማግኘት እና ነፃነትን ለመፈለግ መቁረጥ ኩራት ነው:: ምን አለፋችሁ ቁጭ ብለን ካሰብነው ኩራት ትንሽም ብትሆን እየወሰድናት ያለችው ቆራት ውሳኔ ናት::
ኩራታችሁን ፈልጉት በሽ ነው!
መልካም የኩራት ወር