Skip to content Skip to footer

የኩራት ወር: “ነገር ግን ራስን መቀበል እና ኩራት ከምትኖርበት ቦታ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተምሬአለሁ”

የኩራት ወር ሁል ጊዜ አሁን በአውሮፓ ስለምትኖር ጓደኛዬ እንዳስብ ያደርገኛል። አዲስ አበባ እያለች በጣም ደፋር ነበረች። የሴት ጓደኛ ነበራት፣ እና በግልጽ ፍቅረኛሞች መሆን ባይችሉም አብረው ህይወት መገንባት እንደሚፈልጉ ግልጽ ነበር – የወደፊት እቅድ ያወጣሉ፣ ልጅ መውለድ እንደሚፈልጉ ጭምር ይናገሩ ነበር።

ወደ አውሮፓ ከሄደች በኋላ ግን ሁሉም ነገር ተለውጠ። አሁን ሌዝቢያን መሆን “ሀጢያት” ነው ትላለች። ከአሁን በኋላ ከሌሎች ሌዝብያን ወይንም ጌይ ኢትዮጵያውያን ጋር መነጋገር እንደማትፈልግ ትናገራለች። ስለኛ ስለምታውቀን ሰዎች ልትናገር ትችላለች ብለንም እንፈራ ነበር።

በርግጥ እንደ አውሮፓ ያሉ የኛን ማህበረሰብ የሚቀበሉ አገሮች ላይ መኖሯ የበለጠ በነፃነት እንድትኖርና እራሷን የበለጠ እንድትቀበል እንደሚረዳት ነበር የጠበኩት። ነገር ግን ራስን መቀበል እና ኩራት ከምትኖርበት ቦታ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተምሬአለሁ። እውነተኛ ኩራት ምንም ይሁን ምን ከማንነትህ ጋር ደህና መሆን ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የምኖር ሌዝቢያን ሴት በመሆኔ እኮራለሁ። ኩራት ሌሎች ስለሚያስቡት ማሰብ ወይንም መጨነቅ አይደለም – ራስን መውደድ ነው። በዚህ የኩራት ወቅት፣ እውነተኛ ማንነቴን አከብራለሁ። መልካም የኩራት ወር።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading