Skip to content Skip to footer

የኩራት ወር: “አንድ ቀን የቀስተደመናውን ባንዲራ በአደባባይ አዲስ አበባ ላይ እንደምናውለበልብ አስባለሁ”

የኩራት ወር ግራ የሚያጋባኝ ጊዜ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ የምትኖር ሌዝቢያን እንደመሆኔ መጠን እዚህ ምንም የተለየ ነገር አይፈጠርም። ሕይወት እንደ ሌላ ጊዜ ነው። የቀስተ ደመና ባንዲራዎች፣ የኩራት ሰልፎች፣ ወይም ሰዎች ምልካም ኩራት ብለው ሲመኙልን አናይም።

በሌላ በኩል፣ በአለም ውስጥ በሁሉም ቦታ የሚከናወኑትን ሁኔታዎችን እና ሰዎች የሚሰማቸውን ደስታ ሳይ ደስ ይለኛል። ቲክ ቶክ እና ፌስቡክ ከተለያዩ ሀገራት በሚወጡ ነገሮች ተሞልተዋል። ያ ደስተኛ ያደርገኛል እናም በኢትዮጵያም ተስፋ እንዳለን እንዲሰማኝም ያደርግኛል። ተስፋዬ አንድ ቀን እዚህ አዲስ አበባ የኩራት ሰልፍ እንደምናደርግ ወይንም በሆነ ሁኔታ ኩራትን እንደምናከብር ነው። ያ ብዙ ጊዜ የሚወስድ ይመስለኛል ግን አንድ ቀን እንደሚሆን ልቤ ይነግረኛል።

ስለዚህ ጉዳይ ከሌዝቢያን ጓደኞቼ ጋር እንነገገራለን እና አንዳንዶቹ ይህ እንደሚሆን ይስማማሉ ሌሎች ግን ይህን ማሰብ ሞኝነት እንደሆነና በፍፁም የማይሆን ነገር እንደሆነ ይናገራሉ። አንድ ቀን የቀስተደመናውን ባንዲራ በአደባባይ አዲስ አበባ ላይ እንደምናውለበልብ አስባለሁ። ነገሮች ይሻሻሉ ብዬ ማመኔ የበለጠ ተስፋ ይሰጠኛል፤ ያበረታታኛልም። ያ እስኪሆን ድረስ እራሴን እንደ ሌዝቢያን በመቀበሌ እና ከጌይ እና ከሌዝቢያን ጓደኞቼ ጋር ግልጽ መሆን በመቻሌ ኩራት ይሰማኛል። እነሱ የእኔ ቤተሰብ ናቸው።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading