አሁን በአፍሪካ ስለ LBQ መብቶች ምን እንደሚሰማ ማወቅ ከባድ ነው። በዚህ የተስፋ ብልጭታ እና በከፍተኛ ብስጭት መካከል ልቤ ያለማቋረጥ ይጨነቃል።

ኬንያን ብቻ እንመልከት። እዚያ ያለ አንድ ዳኛ ትራንስጀንደር ሰዎች ህጋዊ እውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ወስኗል። ይህ የማይታመን ነው ተስፋ ከሰጡኝ ነገሮች ውስጥ ይመደባል። አንድ ላይ ቆመን ድምፃችንን ስናሰማ ተራሮችን በእውነት እንደምናንቀሳቅስ ማረጋገጫ ነው።
ነገር ግን በዚያው ጊዜ ስለ ቡርኪናፋሶ አነበብኩ። ኩዊርነትን የሚያስቀጣ ሕግ አእንዳወጡ እና ይህን ማንበብ ልክ በዱላ የተመታሁኝ ያህል ነው ያመመኝ። በአንድ ቦታ ላይ እድገትን እያከበርን ሳለ ሌሎች እየተገፉ፣ ህልውናቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ እንደሆነ ማወቅ በጣም አሳዛኝ ነው። በጣም ተስፋ ያሳጣል።
ይህ ሮለርኮስተር በጣም አድካሚ ነው፣ ግን የሚገርመው፣ ትግሉን እንድቀጥል የሚያደርገኝም ይህ ነው። በዚህ ውጊያ ውስጥ ሁላችንም በአንድነት እንደቆምን ያስታውሰኛል። እያንዳንዱ ትንሽ ድል፣ ልክ በኬንያ እንደነበረው፣ ለአንድ ሀገር ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የተስፋ ጭላንጭል ነው። ያበረታታናል።
የማህበረሰባችንን ጥንካሬ ያበረታታኛል። በተቃውሞ ላይ መሳተፍ፣ለሚታገል ሰው ድጋፍ መስጠት፣ ወይም በቀላሉ እውነታችንን መናገር … እያንዳንዳችን ሚና አለን። ከፊት ያለው መንገድ ረጅም ነው፣ ብዙ እንቅፋቶችን እንደሚያጋጥመን ጥርጥር የለውም። ግን ጠንክረን መጠበቅ እና እርስ በርስ መደጋገፍ አለብን። ሁላችንም በነፃነት እና ያለ ፍርሃት የምንኖርበት የወደፊት ጊዜ እውን እንደሚሆን በእውነት አምናለሁ። ተግተን ወደዚያ ጉዟ እንቀጥላለን።