
እናያችኋለን፣ እንሰማችኋለን፣ እናም እኛም ከእናንተ ኢትዮጵያዊ ኩዊር ወገኖቻችን እና ቤተሰባችን ጋር ቆመናል። የፈለግነውን ሰው በመውደዳችን እና እራሳችንን በመሆናችን የሚገጥመንን ከባድ አደጋ እናውቃለን። ኩዊር በመሆናችን የሚደርስብን ሆሞፎቢያ፣ ባይፎቢያ፣ ትራንስፎቢያ እና መድልዎ ልብ የሚሰብር ነው።
ምንም እንኳን እኛ ሙሉ በሙሉ ግልፅ መሆን ባንችልም፤ ዝምታን ግን አንቀበልም። ኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ አሁንም የጥቃት እና የመገለል ኢላማዎች ናቸው። እነዚያ ኢ-ፍትሃዊ ህጎች መብታችንን የሚጥሱት ከመታገል በፍጹም አናቆምም።
እንደ ጥብቅ ትስስር እናዳለው የኩዊር እና ትራንስ ማህበረሰብ ጥላቻንና አድልዎን በጋራ እንቃወማለን። ድፍረትችሁን አይተናል፣ ጽናታችሁን እናደንቃለን፣ እና እርስ በርስ ለመደጋገፍ ያላችሁን ቁርጠኝነት እናደንቃለን።
በአሁን ባለንበት ጊዜ በግልጽ ለውጥን ልንጠይቅ አንችልም፤ ግን ማየት የምንፈልገውን ለውጥ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመር እንችላለን። የደህንነት እና የአብሮነት ቦታዎችን መፍጠር እንቀጥል – በተለይም በአለም አቀፍ የፀረ ሆሞፎቢያ፣ ባይፎቢያ እና ትራንስፎቢያ ቀን። ያለንን ቦታዎች እና አቅሞች እንካፈል፣ እንደጋገፍ እና ለየራሳችን ድምፅ እንሁን።
የእኛ ኩዊር እና ትራንስ ማህበረሰብ ለእኩልነት፣ ለነፃነት እና ለፍትህ ያላቸው ቁርጠኝነት የማይበጠስ ነው። ሁላችንም በነጻነት እና በእውነተኛነት መኖር ይገባናል። በአንድነት ትግሉን እንቀጥል። ዓለም እኛን ለመስበር ሊሞክር ይችላል, ነገር ግን ፍቅራችን እና ጽናታችን ሁልጊዜ ጠንካራ ይሆናል።