በኢትዮጵያ ተመሳሳይ ፆታ ጠልነት በጣም እየጨመረ ቢሄድም ኩራታችን በድፍረት እራሳችንን ሆኖ መኖር ነው፣ ምንም እንኳን በድብቅ መኖር ቢኖርብንም። በማስተዋል ህይወታችንን መኖር መቻል የኩራታችን አንዱ መገለጫ ማለት ነው። እራሳችንን በመሆናችን፣ እርስ በርስ በመዋደዳችን እና በመደጋገፋችን እና የራሳችንን ምቹ ቦታዎችን መፍጠር በመቻላችን እንኮራለን። ሁልጊዜም ባንታይም በዝምታ ራሳችንን መሆናችን ተመሳሳይ ፆታ ጠልነትን መቃወሚያ አንዱ መንገዳችን ነው። በዚህ የኩራት ወር፣ ማንነታችንን በራሳችን መንገድ ህልውናችን እና ውበታችንን እናከብራለን።
