Skip to content Skip to footer

ሲሞን ንኮሊ – አካታች ኩራት

በዚህ የኩራት ወር፣ በአፍሪካ ውስጥ ለLGBTQ+ መብቶች እና የነፃነት ትግል ትልቅ ሚና የተጫወተውን ደቡብ አፍሪካዊ አክቲቪስት ሲሞን ንኮሊ ህይወት እና ትሩፋት እናከብራለን። ንኮሊ ከመጀመሪያዎቹ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ እና ጸረ-አፓርታይድ አራማጆች አንዱ ብቻ ሳይሆን የ GLOW (የጌይ እና ሌዝቢያን ድርጅት ኦፍ ቪትስዋተርስራንድ) መስራች አባል ነው ፤ በደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው በጥቁር የሚመራ የኩዊር መብት ንቅናቄ ነበር። 

የእሱ እንቅስቃሴ ከአፓርታይድ ጋር የሚደረገውን ትግል እና የኩዊር የነጻነት ትግልን አጣምሮ ያሳየን ሲሆን ይህም ፍትህ ሁሉንም ድምጽ ካላካተተ በስተቀር የተሟላ እንዳልሆነ ለአለም አስታውሷል። 

ከሌሎች ፀረ-አፓርታይድ መሪዎች ጋር ታስሮ ጌ ሆኖ መውጣቱ የብዙዎችን አእምሮ የቀየረ እና ሁሉን አቀፍ ተቃውሞ መንገድ የቀየሰ ትልቅ ተግባር ነው።

“ጥቁር ነኝ:: የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወንድ ነኝ:: ሁለቱን ነጣጥዬ ማየት አልችልም። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጥቁር ስለሆንኩ እና  የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወንድ ስለሆንኩ እጨቆናለሁ።”

ኩራትን ስናከብር፣ ሲሞን ንኮሊን እንደታሪካዊ ብቻ ሳይሆን ዛሬም ለአክቲቪስቶች መንገዱን ማብራት መወጠሉን እናስታውሰዋለን። ኩራት መሰረቱ ምከታ እና ትግል መሆኑን እና የምንደሰትባቸው ነጻነቶች የተቀረጹት ከእኛ በፊት በነበሩት ሰዎች ድፍረት መሆኑን ህይወቱ ያስታውሰናል። ሆን ብሎ ማንነታችንን ከታሪክ ለማጥፋት በሚሞከር አለም ውስጥ ለመታየት የደፈሩትን ንኮሊን እና ስፍር ቁጥር የሌላቸውን (ስማቸው ያልተጠቀሰ እና ያልተገለፀ ሁሉ) እናከብራለን። የነሱ ትሩፋት በየቦታው ላለን ሁሉ የነፃነት ትግላችንን ያቀጣጥላል።

መልካም የኩራት ወር

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading