እንኳን በአእምሮ ጤና ላይ ወደሚያተኩረው የንስንስ ዘጠነኛ እትም በደህና መጣችሁ::
ማህበረሰባችን ላይ ያተኮረ ኃይለኛ የጥላቻ ማዕበል በቅርቡ አናውጦ ነበር። አንድ ፀሃፊያችን እንደተናገሩት፣ “እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ጠልነት አጋጥሞን አያውቅም”። በጣም ግላዊ ሆኖ ተሰምቶናል፣ እና ብዙዎቻችን የተለያየ ሃፍረት ስሜቶች፣ ድብርት፣ መገለል፣ ቁጣ፣ ጭንቀት እና መተማመን ማጣትን ጨምሮ ብዙ የአእምሮ ጤና ችግሮች ገጥሞናል።
ጽናታችንን ብንቀጥልም ስለነበረው ሁሉ ማውራት ብቻ ሳይሆን ወደፊትም እራሳችንን እና እርስ በርሳችን የምንረዳዳበትን መንገድ መፈለግ አስፈላጊ ነው።
መስከረም 29 የሚከበረው የአለም የአእምሮ ጤና ቀን መሪ ሃሳብ እንደሚያስታውሰን የአእምሮ ጤና ሁለንተናዊ ሰብአዊ መብት ነው። ይህች የንስንስ እትም እርስ በርስ ለመተሳሰብና ለመደጋገፍ እንዲሁም በአእምሮ ጤንነታችን ዙሪያ ውይይቶችን እንድንቀጥል ሁላችንንም እንደምታበረታታ ተስፋ እናደርጋለን።
ይህን እትም ስላነበቡ እናመሰግናለን። የእርስዎን አስተያየት መስማት እንፈልጋለን እና በ etqueerfamily@gmail.com ላይ ልትፅፉልን ትችላላችሁ።
ኦንላይን ለማንበብ ወይም ለራስ ለማስቀረት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ::
1 Comment