Skip to content Skip to footer

አንድ ድምፅ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጠልነት አዘል ነገሮችን ቲክቶክ ላይ ማየት የተለመደ ሆኗል። አንዳንዱ ተነስቶ በእኛ ዙሪያ ይዝታል፣ ያፌዛል፣ ይሳደባል፣ የተሳሳተ መረጃን ደረቱን ነፍቶ እንደሳይንሳዊ ግኝት ያቀርባል። ሌላው ደግሞ የማያውቀውን ሰው በምላሽ መስጫው (comment) ላይ እየገባ “ጌ ነህ እናውቃለን” ይላል፣ ያስፈራራል፣ ሌሎችንም እያነሳሳ የደቦ ፍርድ ይጣራል።  

ከጥቂት አመታት በፊት እንዲሁ በተመሳሳይ በፌስቡክ የተጀመረ የጥላቻ ዘመቻ ነበር። የሚገርመው ያኔ ሀገራችን እንደዚህ አይነት ነገር አይገባም የሚል ነበር። ጣቱን ወደሌላው አለም አድርጎ “የድንበር ጠባቂ ያለ” እያለ “ሀገርን መክት” አይነት ጥሪ ነበር። ነገሩ (ዘመቻው) ለኔ አዲስ ስለነበረ ጊዜው ያስፈራ ነበር። ፌስቡክ ላይ መምጣት እስከሚፈራ ድረስ…”ማን ምን አለ?” “ቤተሰብ ጓደኛ ምን ሀሳብ ፃፉ?” የሚለው ጭንቀት ነበረው።

ዛሬ ላይ ጥላቻው ገኖ ቢታይም በሚገርም ሁኔታ በጣም  ብዙ ማንነታቸው እና መልካቸው የማይታዩ በየለቱ በምላሽ መስጫው ላይ ለግላቸው ብቻ ሳይሆን ስለሁላችን መብት የሚሟገቱ ኩዊር ሰዎች እና ደጋፊዎች አሉ። “እኛ ሀገር የለም” ከመባል… “ሊያስፋፉ ነው” ወደመባል  ያሻገሩን… ከዛም ይሄን አውቆ የተኛውን ህዝብ ሳይወድ በግዱ “አሉ” ያስባሉልን። ጥላቻው በጨመረ ቁጥር እንደጤፍ በዝተን በአንድ ድምፅ እንድናብር ያደረጉን። ይመቻችሁ! 

የጥላቻ ፌዝ ሲሆን በፌዝ መልስ ምት ዘጭ! 

የተሳሳተ መረጃ ሲሆን በኩዊር የግል ታሪክ ኩም! 

ገና ደግሞ “ይኸው መብታቸውን አስከበሩ” ላይ እንሻገራለን።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading