ሁለተኛውን ምዕራፍ የኢትዮ ኩዊር ፓድካስት መጀመራችንን ስንገልፅ በደስታ ነው:: በጠየቃችሁን መሰረት በየወሩ ይለቀቅ የነበረውን ቃለ መጠይቅ በየሳምንቱ ለ12 ሳምንታት ለመልቀቅ ተስማምተናል::
እዚህ የሚገኘው የመጀመሪያው ክፍል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለን የLBQ ዴቲንግ ላይ ያጠነጥናል:: የLBQ ማህበረሰብ ቁጥር እንደማነስና የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪይን ጠልነት እንደመኖሩ ዴቲንግ ለኩዊር ሰዎች ተግዳሮት እና አደጋ አለው::
በዚህ ዙሪያ ከአራት LBQ ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረግነውን ውይይት ያድምጡ፤ በቃለ መጠይቁ ላይ እንዴት LBQ ማህበረሰቦች እንደሚገናኙ ፣ የአጭር ጊዜ ግንኙነት ባህል ፣ የረዥም ጊዜ የፍቅር ግንኙነት እና ግንኙነቶች ላይ ያሉ አድሎዎችን ተወያይተናል::
ይህ ውይይት የግንኙነት ደስታዎችን እና እንቅፋቶቻችን ይዟል እንዲሁም የኢትዮጵያ ውስጥ ዴቲንግ ላይ ጠቃሚ ምክሮችን ያካፍላል::
እንደምትወዱት አንጠራጠርም፤ እንደሁልጊዜው አስተያየቶቻችሁን እንጠብቃለን::